በጌታችን በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ የተደረገልን ሥርየትና ዕርቅ ግልጥ ሆኖ የተጀመረው በነገረ ልደት ነው።የጌታችን ልደት በነገረ ድኅነት ትልቅ ስፍራ የያዘና እግዚአብሔር ሰው ሆኖ ዓለምን ያዳነበት ጥበቡ ፍጹም ልዩ መሆኑን ያሳየ ነው።መስተፃርራን የነበሩ ሰማይና ምድር፣ሰውና መላእክት በአንድነት ለምስጋና ታድመዋል።የእረኞች አንደበት ከመላእክት ጋር ለሰማያዊ ምስጋና ብቁ የሆነበት፣ግዕዛን የሌላቸው እንስሳት ሰራኢ መጋቢያችን፣በዘባነ ኪሩቤል በሰማያት የምትገለጥ አንተ ነህ ሲሉ እስትንፋሳቸውን የገበሩለት፣የምድር ነገስታት በስልጣንህ ሽረት በመንግስትህ ህልፈት የሌለብህ የነገስታት ንጉስ አንተ ነህ ሲሉ ወርቅን ለመንግስቱ፣ዕጣንን ለክህነቱ፣ከርቤን ለሕማሙ ዕጅ መንሻ ያበረከቱለት፣ወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ከጻድቁ ዮሴፍ ጋር ያን ልዩ ክብር ያዩበት፤ይህ ልደት በእውነት ልዩ ነው።ቅዱስ ኤፍሬምሶሪያዊ በረቡዕ ውዳሴ ማርያም በጌታ ልደት የተደረገልን ድንቅ የማዳን ስራ በተናገረበት ድርሳኑ እንዲህ ነበር ያለው፦"በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ታላቅ ብርሃን ወጣላቸው፤በቅዱሳን የሚያድር እግዚአብሔር እኛን ለማዳን ልዩ ከሆነች ድንግል ሰው ሆኗልና ኑ ይህንን ድንቅ እዩ፣ስለተገለጠልን ምስጢር ምስጋና አቅርቡ ሰው ያማይሆን ሰው ሆኗልና ቃል ተዋህዷልና ቅድምና የሌለው ሥጋ ጥንታዊ ቀዳማዊ ሆነ፣ዘመን የማይቆጠርለት መለኮት ዘመን ተቆጠረለት።" ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ይህች ቤተልሔም መንግስተ ሰማያትን መሰለች" አለ፤የጌታን ልደት በተናገረበት አንቀጽ።በአባታችን በቀዳማዊ አዳም ምክንያት ያጣናትን ልጅነት ሊሰጠን ዳግማዊ አዳም ክርስቶስ የመንግስተ ሰማያትን የምስጋና ኑሮ በቤትልሔም ገልጧልና።ስለዚህ ነገር ነብየ እግዚአብሔር ሚክያስ "አንቺ ቤተልሔም ኤፍራታ አንቺ ከይሁዳ አእላፍ መካከል ትሆኝ ዘንድ ታናሽ ነሽ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞው ጀምሮ ከዘላለም የሆነ በእሳራኤል ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልና.." በማለት የተነበየውም ስለዚህ ነበር፤ሚክ5፡2 "ወአንቲኒ ቤተልሔም ምድረ ኤፍራታ ኢትቴሃቲ እምነገሥተ ይሁዳ እስመ እምኔኪ ይወጽእ ንጉስ ዘይርዕዮሙ ለህዝብየ እስራኤል" እንዲል ቅዱስ ኤፍሬም።
Friday, January 08, 2016
Wednesday, January 06, 2016
የዓለም ድኅነት በክርስቶስ ልደት
ቤተክርስቲያናችን የምትቀበላቸው አምስት ዓበይት ምስጢራተ ቤተክርስቲያን መኖራቸው የታወቀ ነው።እነርሱም "አምስቱ አዕማደ ምስጢር" በሚል ስያሜ ይጠራሉ። ከእነዚህም ታላላቅ ምስጢራት አንዱ ምስጢረ ስጋዌ ነው። "ምስጢር" የሚለው ቃል በቤተክርስቲያናችን አነጋገር በፍልስፍናዊ ርቀትና በምርምር ሳይሆን፤በእግረ ሕሊና ብቻ ሊደርሰበት የሚቻል ነገር እንደሆነ ይታመናል።ስለዚህ ምስጢረ ሳጋዌ ማለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ቃል ከሰማየ ሰማያት ወርዶ መላውን የሰው ዘር ለማዳን ሲል ከድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው የሆነበት ምስጢር ነው። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆን የሚደነቅ እንጂ የማይመረመር ታላቅ ምስጢር ነው። የእግዚአብሔር ቃል ሰው ሆኖ መላውን የሰው ዘር ከድቀተ አዳም ጀምሮ [5,500]አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ሙሉ በሃጢአት አዘቅት ተጥሎ የቅጣት ማዕበል እየወረደበት፤በእግረ ሰይጣን እየተረገጠ የቁም ሙት ሆኖ ሲኖር እንደዚሁ ቃላት ሊገልጹት ከማይችሉት ኀዘንና ስቃይ፤እንዲሁም ተስፋ መቁረጥ ያድነው ዘንድ ስለተወለደ፤የአባቱን ፈቃድ በመፈጸም የሰውን ደዌና ሕማም ተሸክሞ፤ሥጋን ለብሶ ሰው በሆነም ጊዜ መላው የሰው ዘር በመከራ ይኖር ዘንድ ተነግሮ የነበረው አዋጅ ተሻረ። "አዳም ገብሩ ለዲያብሎስ ሔዋን ዓመቱ ለዲያብሎስ" የሚለውም መዝገብ ተቀደደ፤በኀጢአት ፈንጋይነት ታፍኖ ተሽጦ የነበረው አዳምም ወደ ጥንተ ክብሩ ተመልሷል።
በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆን የእግዚአብሔር መለኮታዊ ፍቅሩ፣ጸጋውና ይቅርታው ተገልጿል። ከፈጣሪው ቅጽረ ረድኤት ውጭ ሆኖ የነበረው አዳም ወደ ጥንተ ቦታውና ማዕረጉ ክብሩና ሞገሱም ተመልሷል። በሰማይና በምድር መካከል የዕርቅና የይቅርታ ሰንደቅ አላማ ተተክሏል። ከፈጣሪው ጋር እንዲሁም ከራሱና ከአካባቢው ጋር ተጣልቶ ይኖር የነበረው ፍጡርም ታርቋል። ይህም ዕርቅ ምን ማለት እንደሆነ ለመግለጽ ያህል ኦሪት ዘፍጥረት3፡23 አዳም የፈጣሪውን መንግሥት ለመገልበጥ ባደረገው አመጽና፡መቀናቀን የሞት ሞት ተፈርዶበት ከገነት ሲወጣ ዱሮ በትእዛዙ ሲተዳደሩ ይኖሩ የነበሩት አራዊትና እንስሳት ሁሉ አፋቸውን ከፍተው አስፈራሩት ቀንዳቸውንም አሹለው ሊወጉት ቃጡ። በጥፍራቸው ኃይል የሚጠቀሙት እንዲሁ ጥፍራቸውን አዘርዝረው ሊቧጥጡት ቀረቡ ይላል። ይህም አዳም ባደረገው ጥፋት ተጣልቶ የነበረው ከእግዚአብሐር ጋር ብቻ ሳይሆን ከአካባቢውም ጋር እንደነበር ያስተምረናል። በተጨማሪም ከዚህ በላይ በወንጀለኛ ላይ የሚፈርደው ዳኛ ብቻ ሳይሆን ጎረቤት ፣ወዳጅና ዘመድና ባዕድም ጭምር እንደሆነ እንረዳለን። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ ከተወለደ በኋላ ግን የሰው ኀዘኑ ወደ ፍሥሐ ተለውጧል።በጠቅላላው ልደተ ክርስቶስ ነገደ አዳምን በሙሉ ከዲያብሎስ ባርነት ነጻ አውጥቶ ከአካባቢውና ከመላው ሥነ ፍጥረት ጋር ከነበረው ቂምና በቀል እንዲሁም ጠላትነት አስታርቆ የራሱንም የሕሊና ባርነት ድል እንዲነሳ አድርጎ የእግዚአብሔር ልጅ ለመሆን አብቅቶታል።
በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆን የእግዚአብሔር መለኮታዊ ፍቅሩ፣ጸጋውና ይቅርታው ተገልጿል። ከፈጣሪው ቅጽረ ረድኤት ውጭ ሆኖ የነበረው አዳም ወደ ጥንተ ቦታውና ማዕረጉ ክብሩና ሞገሱም ተመልሷል። በሰማይና በምድር መካከል የዕርቅና የይቅርታ ሰንደቅ አላማ ተተክሏል። ከፈጣሪው ጋር እንዲሁም ከራሱና ከአካባቢው ጋር ተጣልቶ ይኖር የነበረው ፍጡርም ታርቋል። ይህም ዕርቅ ምን ማለት እንደሆነ ለመግለጽ ያህል ኦሪት ዘፍጥረት3፡23 አዳም የፈጣሪውን መንግሥት ለመገልበጥ ባደረገው አመጽና፡መቀናቀን የሞት ሞት ተፈርዶበት ከገነት ሲወጣ ዱሮ በትእዛዙ ሲተዳደሩ ይኖሩ የነበሩት አራዊትና እንስሳት ሁሉ አፋቸውን ከፍተው አስፈራሩት ቀንዳቸውንም አሹለው ሊወጉት ቃጡ። በጥፍራቸው ኃይል የሚጠቀሙት እንዲሁ ጥፍራቸውን አዘርዝረው ሊቧጥጡት ቀረቡ ይላል። ይህም አዳም ባደረገው ጥፋት ተጣልቶ የነበረው ከእግዚአብሐር ጋር ብቻ ሳይሆን ከአካባቢውም ጋር እንደነበር ያስተምረናል። በተጨማሪም ከዚህ በላይ በወንጀለኛ ላይ የሚፈርደው ዳኛ ብቻ ሳይሆን ጎረቤት ፣ወዳጅና ዘመድና ባዕድም ጭምር እንደሆነ እንረዳለን። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ ከተወለደ በኋላ ግን የሰው ኀዘኑ ወደ ፍሥሐ ተለውጧል።በጠቅላላው ልደተ ክርስቶስ ነገደ አዳምን በሙሉ ከዲያብሎስ ባርነት ነጻ አውጥቶ ከአካባቢውና ከመላው ሥነ ፍጥረት ጋር ከነበረው ቂምና በቀል እንዲሁም ጠላትነት አስታርቆ የራሱንም የሕሊና ባርነት ድል እንዲነሳ አድርጎ የእግዚአብሔር ልጅ ለመሆን አብቅቶታል።
Monday, December 28, 2015
አበጀ በለው(1)
ፀሐይ አያጠቁረው ውርጭ አያከስለው፣
ራብ አያከሳው ጥም አያዝለው፣
ድካም አይሰማው እንቅልፍ አይጥለው ፣
ጎራዴ አያቆስለው ጥይት አይገድለው፣
ስጋ እንዳልለበሰ እንደ ሌላው ሰው፣
ይሄ ሁሉ ጣጣ በሰው ላይ ያለው፣
በሱ አለመኖሩ ምን ይሆን መላው፣
የጀግኖቹ ጀግና አበጀ በለው።
ምነው ባደረገኝ ጋሻ ጃግሬውን፣
ስከተል እንድኖር ኋላ ኋላውን፣
ምነው ባደረገኝ ደበላ ድጉን፣
ወይም ባደረገኝ እጥፍ ዝናሩን፣
ዙሪያ ተጠምጥሜ እንዳቅፍ ወገቡን፣
ምነው ጠመንጃውን ባረገኝ እግዜር
ከደረቱ ሳልወርድ አቅፎኝ እንድኖር።
እዚህ ተቀምጨ ከምኖር በደስታ፣
እረፍት ሳያምረኝ ወገቤን ሳልፈታ፣
አንተን ተከትየ ከጥዋት እስከማታ፣
በጎንቻ በረሀ ልበል ገልታ ገልታ፣
እንቅፋት ሲመታህ አብሬህ ልመታ።
አበጀ በላቸው የመብቴ ጠባቂ ያርነቴ ጌታ።
ምጣዴን አዝዬ እርኮቴን አንግቼ፣
ሽንብራ ቆርጥሜ ጥር ዉሀ ጠጥቼ፣
ራበኝ ደከመኝ ላልል ተገዝቼ፣
ባለ ጸጋ ባሌን ዛሬውን ፈትቼ፣
እሱን እንድከተል ቤት ንብረቴን ትቼ፣
የእግሩ አጣቢ እንድሆን ግርድና ገብቼ፣
አበጀን አማልዱኝ ዘመድ ወዳጆቼ።
የራስ የደጅ አዝማች ምሽት ከመሆኔ፣
አሽከር ከመላኬ ስጋር ከማስጫኔ፣
ስባንን እንድኖር ሳይከደን አይኔ፣
እንቅልፍ እንዳልጠግብ ተኝቼ በጎኔ፣
የእሱ ገረድ ሆኘ ልኖር መለመኔ፣
ወንድ ብወድ ነው ሴት ስለሆንሁ እኔ
ስማኝ ያገሬ ወንድ ልውቀስህ ወቀሳ፣
አይደለህ ቀማኛ አይደለህ ጀውሳ፣
ሳትሰርቅ ሳትቀማ ሳይኖርህ አበሳ፣
እየነዱ ሲያስሩህ እንዲሁ ባፈሳ፣
የማትንፈራገጥ የምትንቀሳሳ፣
ትንሽ የማትሻክር ከሆንክ ለስላሳ፣
በሁለት እግሩ ቆሞ ከሚሄድ እንስሳ፣
ወይም ነፍስ ከሌለው ከወደቀ ሬሳ፣
ከቶ ልዩነትህ በምንላይ ነውሳ።
በነሴና እነብሴ በነማይ በጎንቻ፣
ወንዱ ሁል ሴት ሆኖ ከቀረ አንድ ብቻ፣
ለቀማኞች መቅጫ ላመጸኞች መምቻ፣
ለደካሞች ምሽግ ጋሻ መመከቻ፣
ለእሱ ተሸክሜ ውሃ በቅምጫና ጥሬ በስልቻ፣
እንኳን በማውቀው ዱር በማውቀው ስርቻ፣
ስሄድ አልኖርም ወይ እስ'ካገር ዳርቻ።
ሌሎች ሲበደሉ እሱ መከፋቱ፣
ሌላ ሰው ሲጠቃ እሱ መቆጣቱ፣
የሰው ቁስል አሞት እንዲህ መሰቅየቱ፣
ግፍን እና አመጽን እንደ መርዝ መጥላቱ፣
ህይዎቱን ለሰው መብት ዋጋ አርጎ መስጠቱ፣
ግርማው እንደ አንበሳ ሲያዩት ማስፈራቱ፣
ምን ከባህር አሸዋ ቢበዛም ጠላቱ፣
ጎራዴውን መዞ አውጥቶ ካፎቱ፣
ብቻውን ብቅ ሲል መድረሻ ማጣቱ፣
ሳያሰናክለው ጋራው ቁልቁለቱ፣
ሃይሉን ሳይቀንሰው እራቡ ጥማቱ፣
እርቀት ሳይገታው እንደ'ሳብ ፍጥነቱ፣
እነሴ ነው ሲባል ጎንቻ መታየቱ፣
ይህን ሁሉ ባህርይ ይዞ መገኘቱ፣
አይመሰክርም ወይ ሰው ከተሰራበት
ከጎስቋላ ጭቃ ላለመሰራቱ።
ጥንቱኑ ሲፈጠር ሲወለድ ከናቱ፣
የሰው ቤዛ እንዲሆን ታዞ ለመምጣቱ፣
አየ ምን ያደርጋል በከንቱ መመኘት
የማይገኝ ነገር፣
ባይሆንማ ኖሮ ሹመት እንደቂጥኝ
የሚወረስ በዘር፣
ቅን ፍርድ ለመስጠት ሰው ለማስተዳደር፣
የያንዳዱን ደሃ መብት ለማስከበር፣
ለዚህ ለተጠቃ ለተበደለ አገር፣
መድሃኒት እንዲሆን እሱን መሾም ነበር።
ምንጭ፦ፍቅር እስከ መቃብር
ራብ አያከሳው ጥም አያዝለው፣
ድካም አይሰማው እንቅልፍ አይጥለው ፣
ጎራዴ አያቆስለው ጥይት አይገድለው፣
ስጋ እንዳልለበሰ እንደ ሌላው ሰው፣
ይሄ ሁሉ ጣጣ በሰው ላይ ያለው፣
በሱ አለመኖሩ ምን ይሆን መላው፣
የጀግኖቹ ጀግና አበጀ በለው።
ምነው ባደረገኝ ጋሻ ጃግሬውን፣
ስከተል እንድኖር ኋላ ኋላውን፣
ምነው ባደረገኝ ደበላ ድጉን፣
ወይም ባደረገኝ እጥፍ ዝናሩን፣
ዙሪያ ተጠምጥሜ እንዳቅፍ ወገቡን፣
ምነው ጠመንጃውን ባረገኝ እግዜር
ከደረቱ ሳልወርድ አቅፎኝ እንድኖር።
እዚህ ተቀምጨ ከምኖር በደስታ፣
እረፍት ሳያምረኝ ወገቤን ሳልፈታ፣
አንተን ተከትየ ከጥዋት እስከማታ፣
በጎንቻ በረሀ ልበል ገልታ ገልታ፣
እንቅፋት ሲመታህ አብሬህ ልመታ።
አበጀ በላቸው የመብቴ ጠባቂ ያርነቴ ጌታ።
ምጣዴን አዝዬ እርኮቴን አንግቼ፣
ሽንብራ ቆርጥሜ ጥር ዉሀ ጠጥቼ፣
ራበኝ ደከመኝ ላልል ተገዝቼ፣
ባለ ጸጋ ባሌን ዛሬውን ፈትቼ፣
እሱን እንድከተል ቤት ንብረቴን ትቼ፣
የእግሩ አጣቢ እንድሆን ግርድና ገብቼ፣
አበጀን አማልዱኝ ዘመድ ወዳጆቼ።
የራስ የደጅ አዝማች ምሽት ከመሆኔ፣
አሽከር ከመላኬ ስጋር ከማስጫኔ፣
ስባንን እንድኖር ሳይከደን አይኔ፣
እንቅልፍ እንዳልጠግብ ተኝቼ በጎኔ፣
የእሱ ገረድ ሆኘ ልኖር መለመኔ፣
ወንድ ብወድ ነው ሴት ስለሆንሁ እኔ
ስማኝ ያገሬ ወንድ ልውቀስህ ወቀሳ፣
አይደለህ ቀማኛ አይደለህ ጀውሳ፣
ሳትሰርቅ ሳትቀማ ሳይኖርህ አበሳ፣
እየነዱ ሲያስሩህ እንዲሁ ባፈሳ፣
የማትንፈራገጥ የምትንቀሳሳ፣
ትንሽ የማትሻክር ከሆንክ ለስላሳ፣
በሁለት እግሩ ቆሞ ከሚሄድ እንስሳ፣
ወይም ነፍስ ከሌለው ከወደቀ ሬሳ፣
ከቶ ልዩነትህ በምንላይ ነውሳ።
በነሴና እነብሴ በነማይ በጎንቻ፣
ወንዱ ሁል ሴት ሆኖ ከቀረ አንድ ብቻ፣
ለቀማኞች መቅጫ ላመጸኞች መምቻ፣
ለደካሞች ምሽግ ጋሻ መመከቻ፣
ለእሱ ተሸክሜ ውሃ በቅምጫና ጥሬ በስልቻ፣
እንኳን በማውቀው ዱር በማውቀው ስርቻ፣
ስሄድ አልኖርም ወይ እስ'ካገር ዳርቻ።
ሌሎች ሲበደሉ እሱ መከፋቱ፣
ሌላ ሰው ሲጠቃ እሱ መቆጣቱ፣
የሰው ቁስል አሞት እንዲህ መሰቅየቱ፣
ግፍን እና አመጽን እንደ መርዝ መጥላቱ፣
ህይዎቱን ለሰው መብት ዋጋ አርጎ መስጠቱ፣
ግርማው እንደ አንበሳ ሲያዩት ማስፈራቱ፣
ምን ከባህር አሸዋ ቢበዛም ጠላቱ፣
ጎራዴውን መዞ አውጥቶ ካፎቱ፣
ብቻውን ብቅ ሲል መድረሻ ማጣቱ፣
ሳያሰናክለው ጋራው ቁልቁለቱ፣
ሃይሉን ሳይቀንሰው እራቡ ጥማቱ፣
እርቀት ሳይገታው እንደ'ሳብ ፍጥነቱ፣
እነሴ ነው ሲባል ጎንቻ መታየቱ፣
ይህን ሁሉ ባህርይ ይዞ መገኘቱ፣
አይመሰክርም ወይ ሰው ከተሰራበት
ከጎስቋላ ጭቃ ላለመሰራቱ።
ጥንቱኑ ሲፈጠር ሲወለድ ከናቱ፣
የሰው ቤዛ እንዲሆን ታዞ ለመምጣቱ፣
አየ ምን ያደርጋል በከንቱ መመኘት
የማይገኝ ነገር፣
ባይሆንማ ኖሮ ሹመት እንደቂጥኝ
የሚወረስ በዘር፣
ቅን ፍርድ ለመስጠት ሰው ለማስተዳደር፣
የያንዳዱን ደሃ መብት ለማስከበር፣
ለዚህ ለተጠቃ ለተበደለ አገር፣
መድሃኒት እንዲሆን እሱን መሾም ነበር።
ምንጭ፦ፍቅር እስከ መቃብር
Friday, December 18, 2015
490
መንገደኛው ዛሬ ሽምግልና ተቀምጬአለሁ።ሁለት ላለመስማማት የተስማሙ ጓደኛሞችን ለማስታረቅ ነበር የተቀመጥነው።አብሮ
አደጎች፣አብረው ብዙ ያሳለፉ የጋራ ትዝታዎቻቸው፣የጋራ ደስታቸው፣የጋራ ኀዘናቸው የበረከተ ወዳጆች ነበሩ።ሆኖም አሁን
ግን የተስማሙት ላለመስማማት ነው።አንዱ አንዱ የሚናገረው አይጥመውም፣የሚተያዩት በትዕቢት ዓይን ነው።ክፉኛ
ተናንቀዋል{በሁለቱም ሊተረጎም ይችላል}በየንግግራቸው ውስጥ እንደ አዝማች የሚጠቀሙት ደግሞ "አላውቅህም ወይ?"
የሚል ዜማ አለ።የሚነጋገሩት ላለመረታት ነው።ቆይተው ደግሞ "ጉድህን ነው የማወጣልህ! ጎድህን ነው
የማዝረከርክልህ!" ይባባላሉ።ሁለቱም ጓደኛሞች ግን ማተብ ያሰሩ፣ቤተክርስቲያን የሚስሙ ክርስቲያኖች ነበሩ።የጠባቸው
መንስኤ ተብል የሚቀርበው ነገር እዚህ ግባ የማይባል ተራ ነገር ነው።እንኳን ብዙ ያሳለፉ አብሮ አደጎች በቅርቡ
የተገናኙ ሰዎች እንኳን ሊጣሉ የማይችሉበት ተራ ምክንያት።አንዱ ሲናገር ሌላኛው ስሩ ይገታተራል።"ልብ አድርጉልኝ
እያዋረደኝ ነው! ልታሰድቡኝ ነው እንዴ? የጠራችሁኝ!" ይላል።ተናጋሪው ደግሞ ፊቱ በድል አድራጊነት ያበራል።እኔ
ግን ከተነገሩት ነገሮች የትኛው ስድብ እንደሆነ የትኛው እንደሚያዋርድ አልገባህ ብሎኝ ተቸገርሁ።"በደንብ አልሰማሁ
ይሆን? "ብየም ተጠራጠርሁ።ሆኖም እነርሱ የተግባቡበት ውስጣዊ ቋንቋ ነበር።ነገሩን እንደምንም አብርደን
ልናስታርቃቸው ሞከርን።ሆኖም ላይስማሙ የተስማሙት ጓደኛሞች ቃላችንን ሊሰሙ አልፈለጉም። የእርቅ ጉዳይ ሲነሳ ሁለቱም
ነብሮች ሆኑ።ማሉ ተገዘቱ።"ወይ ክርስትና "አልኩኝ በልቤ።"ጠላቶቻችሁን ውደዱ" የሚለው ቃል ለካ ጥቅስ ብቻ
ነበረ።ቃሉን ለመስማት እንጅ እንደቃሉ ለመኖር የሚፈቅድ ማንም የለም።የማውቀውን መጽሐፍ ቅዱስ ቃል ልናገር ስሞክር
አንድ አንዴ ቀድመው ያብራሩልኛል፣አንደ አንዴ ደግሞ "እርሱ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። አሁን ከዚህ ጋር ምን አገናኘው?"
ይላሉ።አሁን ላይ ያልተጠቀምንባት ወንጌል ለመቼ ልትሆነን ነው?ሁለቱ ስመ እግዚአብሔርን እየጠሩ ማሉ ተገዘቱ።
ዕርቅ የሚሻውን አምላክ ስም ጠርተው አንታረቅም አሉ።ምክንያታቸውን ስንጠይቃቸው "በቃ እንዲሁ ከእርሱ ጋር መቀጠል
አልፈልግም" ከማለት ውጪ ሊታረቁ ላለመቻላቸው አንዳች በቂ ምክንያት አላቀረቡም።ይህን ጊዜ "አለሙን እንዲሁ
ወድዷል" የሚለው ቃል ትዝ አለኝ።እኛን ለመጥላት ብዙ ምክንያት እያለው እንዲሁ የወደደንን አምላክ "እናምናለን"
እያልን እንዲሁ አስጠላኸኝ መባባላችን እንዴት ያሳዝናል።ከሁሉ የገረመኝ አንዳችን ተነስተን ከቃለ እግዚአብሔር
እየጠቀስን ለደቂቃወች ስናወራ በጸጥታ ካዳመጡን በኋላ ንግግራችንን ከምንም ሳይቆጥሩ አቁመው እንዳስቀጠሉት ቴፕ
ያንኑ ንግግራቸውን መቀጠላቸው ነው።
Thursday, December 17, 2015
Tuesday, December 08, 2015
ሰላም
ብላቴናው ወንድማችሁ ሰሞኑን በአንዳንድ የሃገራችን ከተሞችና ዩኒቨርሲቲዎች በተከሰተው አለመረጋጋት ምክንያት ነፍሴ
መረበሽ ከጀመረች ቀናትን አስቆጥሪያለሁ።ነግሩን ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማሁት በጅማ ዞን በሚገኘው የመረዋ ተክለሃይማኖት
ገዳም የሰብል ስብሰባ መርሃ ግብር ስለነበር የበረከቱ ተካፋይ ለመሆን በሄድሁበት ዕለት ነበር።ለ 30 ደቂቃያህል
በቆሎ ስንቃርም ከቆየን በኋላ በብፁዕ አባታችን ትዕዛዝ ስድስት ሰወች ለጤፍ ሸክም እንድንሄድ ተደረገ።በዚህ
ሁኔታ ላይ ሳለን ለአንዱ ጓደኛየ ስልክ ተደውሎለት ለተወሰኑ ደቂቃዎች ሲነጋገሩ ከቆዩ በኋላ በአንድ ግቢ በተከሰተ
ሁከት ምክንያት የሰው ህይወት ማለፉንና የእርሱን ደህንነት ለመጠየቅ እንደደወሉለት ነገረኝ።እውነት ለመናገር መጀመሪያ
ላይ ለጉዳዩ ትኩረት አልሰጠሁትም ነበር።ኧረ! እንዲያውም ተማሪን ለማስደንበር የተፈጠረ ዉሸት መስሎኝ ነበር።ዉሎ
ሲያድር ግን ነገሩ ተጠናክሮ የወሬ ማዕበል ከየአቅጣጫው ይጎርፍ ጀምሯል።አንዱ በእንትና ከተማ ይህን ያህል ሰው
ሲሞት፣ በእንትና ዩኒቨርሲቲ ይህን ያህል ሰው ቆሰለ ይላል። ሌላውም ብድግ አድርጎ "የለም እነዚህ የመንግስት መገናኛ
ብዙሃን ነገሩን ሸፋፍነውት ነው እንጅ የሟቾች ቁጥር ብቻ እንኳን ወደዚህ ከፍ ሳይል አይቀርም" ይላል።የሆነው ሁኖ
ብላቴናውን ፍርሃት ክፉኛ ይንጠኝ ጀምሯል።ምነው ገረማችሁሳ? ወንድ ልጅ አፉን ሞልቶ "ፈራሁ" ሲል ብትስቁም
አይደንቀኝም፤ ምክንያቱም እናንተ የፌደራል ፖሊሶቹን ከስክስ ጫማ ምን እንደሚመስል አታውቁማ።ብታውቁ ኑሮ ግን እንደ እኔ የዶርማችሁን በራፍ በቁም ሳጥን ጥርቅም አድርጋችሁ ዘግታችሁ አልጋችሁን የሙጥኝ ማለታችሁ እንደማይቀር በእርገጠኝነት መናገር እችላለሁ።እኔን ግን ሚገርመኝ
ባልፈራ ነበር።በዚች የቀንበር ቅንጭርት የሰበረ ኮርማ ጭድ ሲሰጠው ቀና በሬ በጅማት ቁግ እየተገረፈ እስከ ማታ
በሚያርስባት፣አጉራ ሰብረው የወጡ ጊደሮች በመላሾ ተደልለው ወደ ጋጣቸው ሲመለሱ ገራም ላሞች ቀፈዳቸው እስኪበር
በሽመል እየተወቁ በሚታለቡባት፣ፍየሎች ተለቀው በጎች በሚኮደኮዱባት፣በእጅ ሚዳሰሰውን የሲኦልን ጨለማ የለበሰ ሰይጣን
በጭብጨባ ሲሸኝ ፀሐይን የተጎናጸፈው የብርሃን መልአክ መከናነቢያውን እንዲያወልቅና እርቃኑን እንዲሄድ
በሚደረግባት፣በርባንን አስፈትታ ክርስቶስን በምታሰቅል፣በዚች እጆቿ በንፁሃን ደም የተጨማለቁባት የአመጸኞች ዓለም
እየኖርሁ መፍራት ይነሰኝ?የመፍራት መብት አንቀፅ ስንት ነበር እባካችሁ?ላለፉት ሁለት ሳምንታት እረፍት ላይ
ስለነበርሁ ጊዜየን ማሳልፈው አንዳንድ አዝናኝ የሆኑ ነገሮችን በማንበብ አልያም በማየት ነበር።ትናንትና
ማታም የጓደኛየን ላፕ ቶፕ ተውሸ "ከቃል በላይ"የተሰኘውን አማርኛ የፍቅር ፊልም እያየሁ በነበረበት ሰዓት ከወደ
ውጭ የመጣ የጩኸት ድምፅ ጭርር... ሲል ሰማሁ።የግቢ ተማሪወች የፌደራል ፖሊስ ሲያዩ የሚያሰሙት ፍርሃት የቀላቀል
የቅዠት ጩኸት ነበር።ፊልሙን እንደምንም ጨርሸ መብራቱድ ድርግም አድርጌ ካጠፋሁ በኋላ ጎኔን ካልጋው ባገናኝም
እንቅልፍ ግን ሊይዘኝ አልቻለም።በምትኩ አእምሮዬ የተለያዩ ጥያቄዎችን እያነሳ ሲያወጣና ሲያወርድ ሌሊቱ
ተገባደደ።ሁከት ምንድን ነው? የሁከት ፈጣሪዋ ማን ነው? አላማውስ ምንድ ነው? ዉጤቱስ? ከሁከት በተቃራኒ ያለው፤
ሰላምስ ምንድ ነው? መገኛውስ ከወዴት ነው? ይህች ዓለም ሰላሟን እንድታጣ የሚደርጓት ነገሮችስ ምንድን ናቸው?እና
የመሳሰሉት።
Thursday, December 03, 2015
የግቢ ማስታወሻ
ሰላምይሁን ተውልዶ ያደገው በባህር ዳር ከተማ ሲሆን የህይወት አስቸጋሪ ውጣ ውረዶችን የጀመረው ገና በሕጻንነት እድሜው እንደሆነ የሚያውቁት ይናገራሉ። ከዕለታት
አንድ ቀን መሐል ፒያሳ ላይ ቆሟል። ምን ማድረግ እንዳለበትም ሆነ የት መሄድ እንዳለበት በትክክል ። መለየት
ተስኖታል። በዚያ ላይ ረሀብ በጣም እያስቸገረው ነው። ሲያስበው ትናንትና ጥዋት ላይ ምግብ ወድ አፉ መጠጋቱ ትዝ
አለው። ያለው ብቸኛ አማራጭ ሁሌም ሰዎች ሲያደርጉት የሚያናድደውን ተግባር እርሱም መፈጸም እንደሆነ አመነበት። እናም ከአራዳ ጊዮርጊስ ወደ መብራት ኃይል ሕንፃ በሚወስደው የግራ መስመር ላይ ቆሞ ታክሲ ለመሳፈር ከሚጋፉት ሰዎች
አጠገብ ደረሰ። ልቡ በአፉ በኩል ወጥታ ለመሄድ የምትታገለው እስኪመስለው ድረስ ፍርሃት እየናጠው ታክሲ ጥበቃ አጠገቡ
የቆመውን ሰው ማናገር ጀመረ። ግን ገና ፊቱ ለመለመን መዘጋጀቱን በሚያሳይ ሁኔታ ሲቅለሰለስበት "እግዚአብሔር
ይስጥህ" ብሎት ቦታ ቀየረ። አሁን ሰላምይሁን አይኖቹ እንባ አቀረሩበት በዚህ መንገድ መለመን ከቀጠለ ማንም ምላሽ
እንደማይሰጠው ወዲያውኑ ተገነዘበ። እንደ ምንም ብሎ ወደ ኋላ በማፈግፈግ አንድ ጥግ ላይ ተቀምጦ ቀጥሎ ማድረግ
ያለበትን ነገር ማውጠንጠን ተያያዘ።ጭንቅላቱ መፍትሄን ከመፈለግ ይልቅ "ለምን ይህ ሁሉ በእኔ ላይ ሆነ?" የሚለው ጥያቄ ፋታ ሊሰጠው አልቻለም። ወደ ላይ እና ወደታች የሚራወጡትን የአዲስ አበባ መኪናወች፣የሰዎችን ሩጫና የተደበላለቀውን ጩኸት ሲያስተውል በእርሱ ውስጥ ያሉ የሃሳብ ብዛት በአካል የታዩ መስሎት ፈገግ ማለት አሰኘው። በፊት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በመከራ ጨርሶ ዩኒቨርሲቲ ከገባ በኋላ ሁሉም ነገር ይስተካከላል በማለት ሲመካ የነበረው ነገር ጭራሽ ሁሉም ነገር ተዘበራርቆ ለእርሱ ዩኒቨርሲቲ የምድር ሁሉ መከራ መለማመጃ መሆኑ ሁሌም ይገርመዋል። የሚወዳቸው እናቱ በአስጊ ሁኔታ የኩላሊት በሽተኛ ስለሆኑ ምን ማድረግ እንዳለበት ተስኖታል። እርሱ የጀመረውን የኢንጂነሪንግ ትምህርት ጨርሶ ለመውጣና እናቱን ለመጦር ከሚያልመው የበለጠ ሌላ ተስፋ በህይዎቱ ውስጥ አለኝ ብሎ አስቦ አያውቅም ነበር። አባቱ በድንገተኛ የመኪና አደጋ ምክንያት ለስራ በወጡበት ሳይመለሱ በመቅረታቸው ገና ክርስትና ከተነሳበት ሳምንት ጀምሮ እናቱ በመከራ ነው ያሳደጉት። እናቱ ወ/ሮ ብርሃን ለእርሱ በትክክል የሕይወቱ ብርሃን መሆናቸውን ያምናል፤እርሳቸው ከሌሉ አበቃ! ብርሃኑም ይጠፋል። ይህ ነው የሰላምይሁን ጭንቀት።
Subscribe to:
Posts (Atom)