መዝገበ ርኅራኄ ድንግል ማርያም፣
ወልዳ የሰጠችን የዓለምን ሰላም፣
ለመላእክት እኅት እናት ናት ለዓለም።
ክብርት ናትና አምሳል የሌላት፣
ድንግል ተወለደች በመላክ ብስራት።
ድንግል ስትወለድ በአምላክ ቃልኪዳን፣
የሊባኖስ ጋራ ተሞላች በብርሃን።
ሀሴት አደረግን በፍጹም ደስታ፣
ምስጋናም አቀረብን ለአምላክ በዕልልታ።
የድንግል መወለድ ከእያቄም ከሐና፣
ስንጠብቀው የኖርን ተስፋችን ነውና።
ዘመድም ባታጣ ወዳጅ ቢኖራት፣
ሐና ምትወልድበት አልተገኘም ቤት፣
እንኳን ቤት በረቱን አይሁድ ነፍገዋት፣
በደብር ተወለደች የአምላክ እናት፤
አባቷ ሰሎሞን በቃለ ትንቢት ፣
ንዒ እምሊባኖስ እኅትዬ መርዓት ፣
ብሎ እንደዘመረ እንዳወደሳት።
ምንጭ ፦መዝገበ ታሪክ ክፍል አንድ
ወልዳ የሰጠችን የዓለምን ሰላም፣
ለመላእክት እኅት እናት ናት ለዓለም።
ክብርት ናትና አምሳል የሌላት፣
ድንግል ተወለደች በመላክ ብስራት።
ድንግል ስትወለድ በአምላክ ቃልኪዳን፣
የሊባኖስ ጋራ ተሞላች በብርሃን።
ሀሴት አደረግን በፍጹም ደስታ፣
ምስጋናም አቀረብን ለአምላክ በዕልልታ።
የድንግል መወለድ ከእያቄም ከሐና፣
ስንጠብቀው የኖርን ተስፋችን ነውና።
ዘመድም ባታጣ ወዳጅ ቢኖራት፣
ሐና ምትወልድበት አልተገኘም ቤት፣
እንኳን ቤት በረቱን አይሁድ ነፍገዋት፣
በደብር ተወለደች የአምላክ እናት፤
አባቷ ሰሎሞን በቃለ ትንቢት ፣
ንዒ እምሊባኖስ እኅትዬ መርዓት ፣
ብሎ እንደዘመረ እንዳወደሳት።
ምንጭ ፦መዝገበ ታሪክ ክፍል አንድ
No comments:
Post a Comment