Tuesday, May 30, 2017

ወአንትሙሰ ንበሩ ሀገረ ኢየሩሳሌም


“ወአንትሙሰ ንበሩ ሀገረ ኢየሩሳሌም እስከ ትለብሱ ኃይለ እምአርያም።እናንተ ግን ከሰማይ ኃይልን እስክትለብሱ ማለትም ሰማያዊ ሃብትን ሰማያዊ እውቀትን ገነዘብ እስከምታደርጉ ድረስ በኢየሩሳሌም ኑሩ ሉቃ፦24:49። ይህ ዶግማ ነው ወገን! ሰማያዊ ሃብት መንግስተ ሰማያትን ገንዘብ እስከምናደርግ ድረስ በኢየሩሳሌም(በቤተክርስቲያን ጥላ ስር) መቆዬት። የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ከሚወርድባት ከማርቆስ እናት ቤት አለመጥፋት።” ዲ/ን ጌታቸው ቢሰጠኝ። 

“የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ማደሪያዎችህ እንደምን የተወደዱ ናቸው! ነፍሴ የእግዚአብሔርን አደባባዮች ትወድዳለች ትናፍቅማለች፤ ልቤም ሥጋዬም በሕያው አምላክ ደስ ተሰኘ።ወፍ ለእርስዋ ቤትን አገኘች፥ ዋኖስም ጫጩቶችዋን የምታኖርበት ቤት አገኘች፤ የሠራዊት አምላክ ንጉሤም አምላኬም ሆይ፥ እርሱ መሠዊያህ ነው። በቤትህ የሚኖሩ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው፤ ለዓለምና ለዘላለምም ያመሰግኑሃል።አቤቱ፥ እርዳታው ከአንተ ዘንድ የሆነለት፥ በልቡም የላይኛውን መንገድ የሚያስብ ሰው ምስጉን ነው።በልቅሶ ሸለቆ ውስጥ በወሰነው ስፍራ የሕግ መምህር በረከትን ይሰጣልና።ከኃይል ወደ ኃይል ይሄዳሉ፤ የአማልክት አምላክ በጽዮን ይታያል። 

የሠራዊት አምላክ አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማ፤ የያዕቆብ አምላክ ሆይ፥ አድምጥ።አቤቱ፥ መታመናችንን እይልን፥ ወደ ቀባኸውም ፊት ተመልከት።ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮችህ አንዲት ቀን ትሻላለች፤ በኃጥኣን ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ በእግዚአብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥሁ።መዝ 83፦1-10።”

የ2009ዓ.ም የጅ/ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉ ምክክር ንዑስ ክፍል አባላት ከሻይ መርሃ ግብር መልስ በአለን ደብረገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ግንቦት 19/2009 ዓ.ም።

No comments:

Post a Comment