Sunday, May 07, 2017

ሰምታችኋል???


አልሰማንም እንዳትሉ! ያልሰማችሁ ስሙ! ይህ ትላንት ሚያዚያ 28 ቀን 2009 ዓ.ም የጅማ ዩኒቨርሲቲ  ዋና ግቢ ግቢ ጉባኤ 26ኛ ዓመት የምስረታ በዓልንና  የጅማ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤቷ የከበረበትን 10ኛ ዓመት ክብረ በዓል ምክንያት በማድረግ “ህይወት በግቢ ጉባኤ ቆይታና ከግቢ ውጪ” በሚል ርዕስ በተዘጋጀው የምክክር መድረክ ላይ የተላለፈ የመጨረሻው መልእክት ነው።

“እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው። የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ። እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ የእምነትን መጠን እንዳካፈለው፥ እንደ ባለ አእምሮ እንዲያስብ እንጂ ማሰብ ከሚገባው አልፎ በትዕቢት እንዳያስብ በመካከላችሁ ላለው ለእያንዳንዱ በተሰጠኝ ጸጋ እናገራለሁ።

በአንድ አካል ብዙ ብልቶች እንዳሉን፥ የብልቶቹም ሁሉ ሥራ አንድ እንዳይደለ፥ እንዲሁ ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን፥ እርስ በርሳችንም እያንዳንዳችን የሌላው ብልቶች ነን። እንደ ተሰጠንም ጸጋ ልዩ ልዩ ስጦታ አለን፤ ትንቢት ቢሆን እንደ እምነታችን መጠን ትንቢት እንናገር፤ አገልግሎት ቢሆን በአገልግሎታችን እንትጋ፤ የሚያስተምርም ቢሆን በማስተማሩ ይትጋ፤  የሚመክርም ቢሆን በመምከሩ ይትጋ፤ የሚሰጥ በልግስና ይስጥ፤ የሚገዛ በትጋት ይግዛ፤ የሚምር በደስታ ይማር። ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን።

ክፉውን ነገር ተጸየፉት፤ ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ፤  በወንድማማች መዋደድ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፤ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ፤ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ለጌታ ተገዙ፤ በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ፤  ቅዱሳንን በሚያስፈልጋቸው እርዱ፤ እንግዶችን ለመቀበል ትጉ።  የሚያሳድዱአችሁን መርቁ፥ መርቁ እንጂ አትርገሙ። ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፥ ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ።  እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ተስማሙ፤ የትዕቢትን ነገር አታስቡ፥ ነገር ግን የትሕትናን ነገር ለመሥራት ትጉ። ልባሞች የሆናችሁ አይምሰላችሁ። 

ለማንም ስለ ክፉ ፈንታ ክፉን አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ።  ቢቻላችሁስ በእናንተ በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ።  ተወዳጆች ሆይ፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፥ ለቍጣው ፈንታ ስጡ እንጂ፤ በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፎአልና። ጠላችሁ ግን ቢራብ አብሉት፤ ቢጠማ አጠጡት፤ ይህን በማድረጋችሁ በራሱ ላይ የእሳት ፍም ትከምራላችሁና።  ክፉውን በመልካም አሸንፉ እንጂ በክፉ አትሸነፉ። ሮሜ12፦1-21“

ይህንን መልዕክት ያስተላለፈው  ወንድማችን ዲያቆን ዳዊት እና ባለቤቱ ወይዘሮ የውብዳር በዚሁ ዕለት 10ኛ ዓመት የጋብቻ በዓላቸውን በቦታው ተገኝተው በደስታና በደማቅ ሁኔታ አክብረዋል። እኔም በቅናት መንፈሳዊ እርር ድብን ስል አመሻሽቼ እግዚአብሔር የመረጣቸው ፍቅሩና ስጦታው የበዛላቸው ጥንዶች ብያቸዋለሁ።
መልካም ዕለተ ሰንበት!!!

No comments:

Post a Comment