ቤተክርስቲያናችን የምትቀበላቸው አምስት ዓበይት ምስጢራተ ቤተክርስቲያን መኖራቸው የታወቀ ነው።እነርሱም "አምስቱ አዕማደ ምስጢር" በሚል ስያሜ ይጠራሉ። ከእነዚህም ታላላቅ ምስጢራት አንዱ ምስጢረ ስጋዌ ነው። "ምስጢር" የሚለው ቃል በቤተክርስቲያናችን አነጋገር በፍልስፍናዊ ርቀትና በምርምር ሳይሆን፤በእግረ ሕሊና ብቻ ሊደርሰበት የሚቻል ነገር እንደሆነ ይታመናል።ስለዚህ ምስጢረ ሳጋዌ ማለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ቃል ከሰማየ ሰማያት ወርዶ መላውን የሰው ዘር ለማዳን ሲል ከድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው የሆነበት ምስጢር ነው። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆን የሚደነቅ እንጂ የማይመረመር ታላቅ ምስጢር ነው። የእግዚአብሔር ቃል ሰው ሆኖ መላውን የሰው ዘር ከድቀተ አዳም ጀምሮ [5,500]አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ሙሉ በሃጢአት አዘቅት ተጥሎ የቅጣት ማዕበል እየወረደበት፤በእግረ ሰይጣን እየተረገጠ የቁም ሙት ሆኖ ሲኖር እንደዚሁ ቃላት ሊገልጹት ከማይችሉት ኀዘንና ስቃይ፤እንዲሁም ተስፋ መቁረጥ ያድነው ዘንድ ስለተወለደ፤የአባቱን ፈቃድ በመፈጸም የሰውን ደዌና ሕማም ተሸክሞ፤ሥጋን ለብሶ ሰው በሆነም ጊዜ መላው የሰው ዘር በመከራ ይኖር ዘንድ ተነግሮ የነበረው አዋጅ ተሻረ። "አዳም ገብሩ ለዲያብሎስ ሔዋን ዓመቱ ለዲያብሎስ" የሚለውም መዝገብ ተቀደደ፤በኀጢአት ፈንጋይነት ታፍኖ ተሽጦ የነበረው አዳምም ወደ ጥንተ ክብሩ ተመልሷል።
በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆን የእግዚአብሔር መለኮታዊ ፍቅሩ፣ጸጋውና ይቅርታው ተገልጿል። ከፈጣሪው ቅጽረ ረድኤት ውጭ ሆኖ የነበረው አዳም ወደ ጥንተ ቦታውና ማዕረጉ ክብሩና ሞገሱም ተመልሷል። በሰማይና በምድር መካከል የዕርቅና የይቅርታ ሰንደቅ አላማ ተተክሏል። ከፈጣሪው ጋር እንዲሁም ከራሱና ከአካባቢው ጋር ተጣልቶ ይኖር የነበረው ፍጡርም ታርቋል። ይህም ዕርቅ ምን ማለት እንደሆነ ለመግለጽ ያህል ኦሪት ዘፍጥረት3፡23 አዳም የፈጣሪውን መንግሥት ለመገልበጥ ባደረገው አመጽና፡መቀናቀን የሞት ሞት ተፈርዶበት ከገነት ሲወጣ ዱሮ በትእዛዙ ሲተዳደሩ ይኖሩ የነበሩት አራዊትና እንስሳት ሁሉ አፋቸውን ከፍተው አስፈራሩት ቀንዳቸውንም አሹለው ሊወጉት ቃጡ። በጥፍራቸው ኃይል የሚጠቀሙት እንዲሁ ጥፍራቸውን አዘርዝረው ሊቧጥጡት ቀረቡ ይላል። ይህም አዳም ባደረገው ጥፋት ተጣልቶ የነበረው ከእግዚአብሐር ጋር ብቻ ሳይሆን ከአካባቢውም ጋር እንደነበር ያስተምረናል። በተጨማሪም ከዚህ በላይ በወንጀለኛ ላይ የሚፈርደው ዳኛ ብቻ ሳይሆን ጎረቤት ፣ወዳጅና ዘመድና ባዕድም ጭምር እንደሆነ እንረዳለን። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ ከተወለደ በኋላ ግን የሰው ኀዘኑ ወደ ፍሥሐ ተለውጧል።በጠቅላላው ልደተ ክርስቶስ ነገደ አዳምን በሙሉ ከዲያብሎስ ባርነት ነጻ አውጥቶ ከአካባቢውና ከመላው ሥነ ፍጥረት ጋር ከነበረው ቂምና በቀል እንዲሁም ጠላትነት አስታርቆ የራሱንም የሕሊና ባርነት ድል እንዲነሳ አድርጎ የእግዚአብሔር ልጅ ለመሆን አብቅቶታል።