Wednesday, March 29, 2017

“ነው ብሎ ቢነግህ እህ.....? ጨምርበት”

“ነው ብሎ  ቢነግህ እህ.....? ጨምርበት” ይላል የሀገሬ ሰው ከደቂቃዎችበፊት አንድ ጓደኛዬ facebook ላይ አገኘኝና የሚከተለውን መልእክት ላከልኝ ።
“የእመቤታችን የቅድስት ድንንግል ማሪያም መልዕክት::በአውሮፖውያን አቆጣጠር በ 1994 ዓ.ም 2ኛ ወር ላይ በክፍለ ሀገር በየጉላቪያ ጠንክራ የሆናችሁ ልጆች ዛሬ ላመሰግናችሁ ለጸሎታችሁ ስለገባችሁት ጦርነት ተጀምሮ እስኪጨርስ ካጠገባችሁ ነኝ ፡፡ ለሁላችሁም ለእያንዳንዳችሁ እባካችሁ በርትታችሁ ከ እግዛብሄር እናንተም ፀልዩ /3 ጊዜ/ በቅዱስ ዮኀንስ ማርቆስ ሎቃስ ማቴዎስ
አባታችን ሆይ በሰማያት የምትኖር ስምህ ይቀደስ መንግስትህ ትምጣ ፍቃድህ በሰማያት እንደሆናቺ እንዲሁም በምድር ላይ ትሁን የእለት እንጀራችንን ስጠን ዛሬ በደላችችንን ይቅር በለን እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል አቤቱ ወደ ፈተናም አታግባን ከክፍ ሁሉ አድነን እንጂ መንግስተ ያንተ ናትና ኀይል ክብር ምስጋና ለዘላለሙ አሜን፡፡

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ሆይ በ መላኩ በ ቅዱስ ገብርቄል ስላምታ ስላም እልሻለሁ በሀሳብሽ ድንግል ነሽ በስጋሽም ድንግል ነሽ የ አሽናፌ የ እግዛብሄር እናት ሆይ ስላምታ ላንቺ ይገባሻል ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ አንቺ የተባርክሽ ነሽ ጸጋን የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ልዑል እግዛብሄር ከአንቺ ጋር ነውና ከተወደደው ልጂሽ ከጌታቺን ከመድኃኒታቺን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታና ምህርትን ለምኝልን ኃጤታችንን ያስተርሰርይልን ዘንድ ለዘላለሙ አሜን / 3 ጊዜ/

ይሄ የሆነበት ቦታ በዞና ሰሜን ኢጣልይ ነው። ይሄንን መልዕክት 24 ጊዜ አባዝቶ ለወገንህ አድርሱ።ከጨርስክ ከ 18 ቀን በኃላ ውጤቱን ውሽት አይምሰላችሁ።

1ኛ ክርሰትና ትባላለች ይህ መልዕክት ደርሷት አነበበችና እንደ መልዕክቱ መሰርት 24 ኮፒ አድርጋ በተነችው ከጨርሰች በኃላ ሚሊዮን ዶላር አገኘች፡፡

2ኛ ኦፒረሪሳት የተባለው እሱም ይህ መልዕክት እንደደርስው ተቀብሎ ቀዶ ጣለው ከዚያን ግዜ ጀምሮ ህይወቱ ተበላሽቶ ኑሮው ተመሰቃቅለ እና ካናዳ ሄዶ ሞተ፡፡

3ኛ ፋራንክ የተባለ ግለሰብ ይህ መልዕክት እንደደርስው 24 ጊዜ እንድታባዛለት ለ ሴክትሪዋ ሰጣት እሷም ለራሷ ወሰዳ 24 ጊዜ አባዝታ ጨርሰች ከዚያ በኃላ የተመሰቃቀለ ኑሮዋም ተስተካከለ፡፡

4ኛ አንዲት የቢሮ ሰራተኛ ይህ መልዕክት ደርሷት ተቀብላ ከርሳች ከ 18 ቀን በኃላ ከስርዋ ተባርርቺ በኃላም አስታወሰቺና ወርቀቱን 24 ጊዜ አባዝታ ካሰራጨቺ በኃላ የተመሰቃቀለ ኑሮዋ ተስተካክሎ ሚሊየነር ሆነቺ፡፡

5ኛ በአዲስ አበባ አካባቢ በቡራዪ ከተማ አንድ ግለሰብ ይህ መልዕክት እንደደርስው 24 ጊዜ አባዝቱ ካሰራጨ በኃላ መኖሪያ ቤት ስርቶ የተመሰቃቀለ ኑሮው ተስተካክሎለታል፡፡ይህ መልዕክት ተተርጉሞ ለመላው አለም መድርስ አለበት፡፡”

በቃ እንደ ዚህ የሚልነው።እና ለምን እንደላከልኝ ስጠይቀው እርሱም ሰው ልኮልኝ ነው አለ። ወዳጆቼ እኔ ግን እላችኋለሁ ማንም የፈለገውን ነገር የሚሞላበት ባዶ ማድጋ አትሁኑ።ለዚህ አይደል እንዴ “ነው” ብሎ ቢነግርህ እህ....? ጨምርበት የተባለው? እውነት ለመናገር እኛስ በfacebook ስሜን አላራባህም ብሎ ህይዎትን የሚያመሰቃቅል ጨካኝ አሊያም ደግሞ ለስሙ like & share ስለዘነበለት  ቢሊዬነር የሚያደርግ ወረተኛ አምላክ አይተንም ሰምተንም አናውቅ። ተወዳጆች ሆይ ይህን ማለቴ ግን የጸሎትን አስፈላጊነት ዘንግቸው እንዳይመስላችሁ።

No comments:

Post a Comment