Tuesday, March 14, 2017

አለቀች!

ያኔ ድሮ ትላንት እኔ ሳልፈጠር፣
አያት ቅድመ አያቴ በኖሩበት ዘመን፣
ድንቅ ሃብት ነበረች በትውፊት ያገኘኋት፣ 
ለእኔ ለልጃቸው በውርስ ያቀበሏት። 
ካላጠፏት በቀር ጨርሳ የማታልቅ፣
ብትበራ ብትበራ መሰልቸት ያማታውቅ፤
ውብ ሻማ ነበረች ለእኔ የተሰጠች፣
ለትንሽ ጎጆዬ ብርሃን የለገሰች ።
በቤቴ ማዕዘን በአንድ ጥግ በኩል፣
ንፋስ እየገባ እያየሁ ዝም ስል፣
ያልደፈንኩት ስተት እየባሰ መጥቶ፣
ድንቅ ስጦታዬን ክፉኛ  አሰቃይቶ፤
ድንገት አንድ ምሽት ብርሃን በሌለበት ፣
ጨረቃ ከዋከብት በማይታዩበት ፣
መታገል ያቃታት ያች ውብ ሻማዬ፣
ቀልጣ ቀልጣ ቀረች ውርሥ ስጦታዬ።

No comments:

Post a Comment