Sunday, March 27, 2016

አንደበት እና ጾም !

የተከበርክ ምላሴ ሆይ፡አርምሞን ገንዘብ አድርግ።አንተም ብዕረ አርምሞ የሚል ቃልን ጽፈህ ልቦናየን ለሚያውከው  ለዓይኔ መልእክት እንዲደርሰው አድርግ።ሥጋየ ፈቃድ በተነሳበት ጊዜ የጌታየን፣የፈጣሪዬን መከራውንና ግርፋቱን አስብ ዘንድ  ልቦናየ ይህን እያሰበ  እንዲበረታ እንዲህ ከሆነ ለዓለማዊ ህይዎት ሙት እሆናለሁ።ሣጋዊ ምኞትና ፍላጎት በነገሰበት ሕይዎት ለ አርባ አቅናት እንደ ጌታ ት ዝዛና ሕግ ልቡናዬን በንጽህና ለመጠበቅ ይቅርታ ለሚያሰጠው ህይዎት የተገባሁ እንድሆን።የ አባቶችን ምክር እቀበላለሁ፣የቅዱሳንን ፍኖት እከተላለሁ በከንፈሮቼ ላይ መዝጊያን አኑር ምክን ያቱም ብዙ መማር ስለሚገባኝ ነው  የምናገራቸውን ቃላርት እመጥን፣ሰውነቴን ለመቆጣጠር እችል ዘንድ፤ አንደበት የነስን ሩጫ ያሳድፋልና ሞገደኛ በሆነ የጻለ ሾተል ሰዎችን የሚገድል ሰው በቀላሉ ትንሽ ቁጥር ያላቸውን ሰዎች ያንበረክካል።ክንፍ ያላትን ከወጋች የንማትነቀለውን የምላስ ጦር የወረወረ ሰው(በ አላማም ያለ አላማም)አላማውን አይስትም።የቀረቡትን ሁሉ ያቆስላል ፤የመረዘውን ሁሉ ይገድላል።በጾም ወራት ሕሌና ፍጹም መረጋጋት ያስፈልገዋል።ከምድራዊ ሃሳቦች ሁሉ የጸዳ ከሰዎች ተለይቶ ብቻውን ከ አምላኩ ጋር የሆነ ሊሆን ይገባል።ሕሊና የኃዘን ደመና ሊያንዣብብበት ይገበዋል። ውጤቱም እርጥበት እንባን የሚያስከትል መራር ኃዘን ነው።


 ታላላቅ ነገሮችን ለመቆጣጠር የሚፈልግ ሰው ትንንሽ ነገሮችን መቆጣጠር ይኖርበታል። የምላሴን ኃይል ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር  ያለብኝ ከንፈሮቸ ምንም አይነት ቃላት እንዳያፈሱ ተስፋ አድርጌ  ለሰው ልጆች መርዙ የማይነቀል ገደይ እንደ ምላስ ያለ የለምና ነው። ምላስ ዘወትር ግልቢያን እንደሚናፍቅ  ከፊት ለፊት ያለውን ሁሉ ቀድሞ ለማለፍ እንደ ሚጋልብ ፈረስ ነው። ምላስ የተዘጋጀ የተደገነ ቀስት ነው። ሁሉን ማየት የሚቻለው ማን ነው? እጅ በአቅራቢያ የሚገኘውን ትንሽ ነገር በቀላሉ ይጨብጣል ፤እግርም ሁሉንም የመሬት ክፍል አይረግጥም፤አይንም ሰሜንና ደቡብን አይመለከትም፤ምላስ ግን የማይደርስበት ቦታ የለም። ምድርን ሁሉ ያካልላል ለነፍሰ ገዳዮችና ጣኦትን ለሚያመልኩ፣ሐሰትን ለሚዎወዱ አድጋ ነው በእብደታቸው ላይ ሌላ እብደት ይጨምርላቸዋልና። የፈጠነን ምላስ ሊያስቆም የሚችል ምድራዊ ኃይል የለም። ለመናገር የቸኮለ ከንፈርንም እንዲሁ ሰውም ቢሆን ውሽንፍርም ቢሆን፣የበረዶ ግግርም ጎርፍም፣ተራራም ቢሆን ባለ ቀስቱ ቅርብ ነው። ቀስቱ የተደገነ ነው፤ቀስቱ በደጋን ላይ ነው። አንድ ጣቱን ደጋን ላይ አድርጎ  አክሮ ቀስቱን ይወረውራል፤በረው የታለመላቸውን አላማ ይመታሉ። ሰማያዊያን ምድራዊያንም ቢሆኑ አያመልጧቸውም። ሕያዋንንም ሙታንንም ያለፉትን የሚኖሩትንና የሚመጡትን ሁሉ ይገድላል። የምላስ ቀስት እንዳይወረወርባቸው የሚጥብቁትንም የማይጠብቁትንም የተጣላቸውንም ወዳጆቹንም አይምርም።


የምላስ ቀስት የራቀውን አቅርቦ የረቀቀውን አግዝፎ የማይመታው ነገር የለም። ማንም የሚቆጣጠረው ቢኖር የመጀመሪያውን ሽልማት ይወስዳል። የግል ሀብቱም ያደርጋታል። ይህች በውድድር ላይ  ያሉ አሸናፊዎች የሚቀበሏት ሜዳሊያ ናትና ። ከንፈር ብዙ አሳፋሪ ነግሮች ይናገራል፤አቀራረቡ የለዘበና ሳቅ ያጀበው ነው። የሌሎችን ቀልብ  የሚሰርቅና ይሁንታ የሚያገኝ፤ሌሎችን የሚያወድስ ሌሎችም የሚያወድሱት  ሰማያዊና መንፈሳዊ ተፈጥሮን የሚያጠፋ በእግዚአብሔር አምሳል የተሰጠን ተፈጥሮ የሚለውጥ ብዙ ምስጢሮችን የሚተፋ፣ባዕድ ለሆኑ ጆሮዎች አዳዲስና እንግዳ ባህርያትን የሚያስተምር ማንኛውንም አይነት መከራ በሰዎች ላይ የሚያመጣ ነው ። ውስጥ ለውስጥ የቁጣ ባቡር እየገሰገሰ ላይ ላዩን ፈገግታ የሚያሳይ ፣ክንፈር የሚናገርው ነገር ልብ ካለው ጋር የማይመሳሰል የውሸትና የሽንገላ ከንፈሮች ሞትን የሚያመጡ ናቸው። ምላስ የሚገነባውን ጠንካራ መከላከያ መናድ የሚቻለው  ማን ነው? ምላስ ከፈለገ አንድን ቤት፣አንድን ቤተሰብ፣ወይም አንድን ከተማ በቅጽበት ብዙ ድካምና ውጣ ውረድ ሳያስፈለገው  በቀላሉ ሊያዋጋ ይችላል። ሕዝቦች አለቃቸውን እንዲጠሉት አለቃም የሚመራውን ህዝብ እንዲጠላ ያደርጋል። ልክ ተጭሮ ብርሃኑ እንደሚቀጣጠል የሰደድ እሣት ጓደኛ ልጅ ፣ቤተሰብ፣ወንድም አለቃ ሚስት ባል ሳይለይ በቀላሉ እርስ በርሳቸው እንዲዋጉ ያደርጋል።ምላስ ደካማውን ጠንካራ፣ኃያሉን ደካማ ፣ኃጢአተኛውን ንጹህ ንጹሁን ኃጢአተኛ ያደርጋል፤መልካሙን ነገር ያጠፋል።መልሶም ያጠፋል።


ምላስ በጣም ትንሽ ነገር ነው ፤ነገር ግን የበለጠ ኃይልን ተላብሷል። እውነት ለመናገር ምላስ አደጋ ነው። በተለይ ሰማያዊ መሥዋዕት ለሚያቀርቡ ለካህናት። የእግዚአብሔር የምስጋና ቃል ስለሆንኩ መልካም በሆነ የከንፈሬ መዓዛ የምስጋና መዝሙርን ፍጥረት ሁሉ በፊቱ ለሚንቀጠቀጡለት  ለእርሱ አቀርባለሁ። ሥጋዊ ፍላጎቴ በውስጤ ለሚፈጥረው እብደት ለቆንጆ ልጅ ውበት አልዘፍንም። ገጣሚዎች በገና ደርዳሪዎች ፣ዘፋኞች ።መኳንንት ጥበበኞች ዘፈን ለደረደሩላት ለእርሷ፤ለታላቁ እግዚአብሔ ግን እዘምራለሁ። ሁሉን አስተካክሎ ለሚመራ በከፍታው ላይ ለሚያበራው ሦስትነቱና አካል ለማምይከፍለው  አንድነቱ ከምስጋና ሁሉ ትልቅ የሆነ ምስጋና አቀርባለሁ ። ከመላእክቱ ጋር ከምስጋና ባሕር እንደሚቀዱት ምስጋና በከንፈሬ አቀርባለሁ። ከዚህ ዓለም ደስታ በእጅጉ ለሚልቀው ፣ለማያልፈው ለዚያኛው ዓለም ደስታ በተስፋ ለምንጠብቀው ሁሉም ወደ አምላኩ ለሚቀርብበት ለዘላለማዊ ታላቅነቱ እዘምራለሁ። በክርስቶስ ኢየሱስ ሰው እንደሆን ለፈጠረኝ መለኮቱን ከሥጋው አዋህዶ እንድመገበው ለፈቀደልኝ፤የሕይዎትን እስትናፍስ እፍ ላለብኝ  ሰማያዊ ሃብትን ሰማያዊ ተፈጥሮን ለሰጠኝ ለእርሱ እዘምራለሁ። በርቀቀ ምስጢሩ ድንቅ በሆነ ጥበቡ  ሰው ሆኘ ተፈጥሪያለሁና ከዚህም የተነሳ ሟች የሆንኩ እኔ ከማይሞተው ጋር ተዛምጃለሁና ለእግዚአብሔር ሕግ ጋት እዘምራለሁ። 


ምድርንና ሰማይን ለፈጠረበት ጥበቡ ስለ እኛ ስለሰው ልጆች ላለው ዘላለማዊ ፍቅር እዘምራለሁ። ስለሚመጣው የፍርድ ቀን እዘምር ዘንድ አንደበት ተሰጥቶኛልና እናንተ ካህናት ተጠንቀቁ ከእኔ ጋር እግዚአብሔርን በአንድ ቃል እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ አድርጉ። ከንፈሬን ንጹህ አድርጌ እጠብቃለሁ። ንጽህና የተሞላ የምስጋና ዝማሬ  (የተወደደ መስዋዕት) እያቀረብኩ አምላኬን ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ። ታላቁ ንጉሥ አምላኬ ከየዋህ ልቦና በመነጨ አንደበት ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ። ከሐሰተኛና ከሌላ የተበላሸ ከንፈርና አእምሮ የምስጋናና የእርቅ ቃል አይወጣምና ፤ከአንድ ምንጭ ጣፍጭና መራር የሆነ ውኃን መቅዳት አይቻልም። ከረጅም ዘመን በፊት እንግዳ የሆነ እሣት ይካህን ልጆች እንደገደለ ሰማሁ፤መስዋዕት ሲያቀርቡ ንጹህ አልነበሩምና በሌላም ወቅት ይህንን ሰማሁ፣የልዑል እግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት የነካ ሰው እንደተቀሰፈ ሰማሁ ። በሰማኋቸው ነገሮች እንቀጠቀጣለሁ። ንጹህ ሳልሆን ሦስትነታቸውን ለማመስገን በመነሳቴ ።ጥላቻና ኃይል የተሞላ ንግ ግርን በሰማሁ ጊዜ ከሕግና ከመለኪያዎች ሁሉ በላይ ሆኖ ሕይወቴ የነበረበትን ዘመን አስባለሁ።በእንዲህ አይነት ን ግ ግር ፍቱን የሆነ መድኃኒት ማምጣት ይቻለኝ ነበርና ነገሮችን ሁሉ በልቤ ጠበቅኋቸው፤በንግ ግር ፈንታ ጥልቅ ተመስጦ ስፍራውን ይዞታል።ከንፈሬ ምን ማለት እንደሚገባኝና እንደማይገባኝ ተምራለች።።ፍጹም ዝምታን መርጣለች ።ምን መናገር እንዳለባትም ታውቃለች።ሁሉንም ነገር በ አርምሞ ለውጨዋለሁ ወደዚያ ወደ ቀደመው ነገር ተመልሼ  አልመጣም የማይገባቸውን የሚናገሩ ሰዎች ይህ ሕግ አሳሪያቸው ይሁን።



                                                                   ምንጭ፦ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኢንዚናዙ
                                                                              ሕይወቱና ትምህርቱ

No comments:

Post a Comment