Wednesday, March 16, 2016

አቤት ቆሻሻ !

በሀገራችን የዘመን አቆጣጠር ከ1980ዎቹ አጋማሽ አስከ1990 ዎቹ አጋማሽ ድረስ አልፎ አልፎ አዲስ አበባ ስታዲየም መግባትን አዘወትር ነበር ። በተለይ ብሔራዊ ቡድናችን ጨዋታ ሲኖረውና ኢትዮጵያ ቡና ከቅዱስ ጊዮርጊስ ግጥምያ ሲኖራቸው አልቀርም ነበር ።ታዲያ በስቴድየሙ ቆይታዬ የሚያረካኝ ከጫወታው ይልቅ ከመስመር ያልወጡ የደጋፊዎች ብሽሽቅ ፣ ቀልድና ትርርብ ነበር ። ከሁሉም ከሁሉም ደስ የማይልና ጋጠወጥ ድርጊት ሲያጋጥም ታዳምያኑ በሙሉ በአንድ ድምጽ የሚያሰሟት የተቃውሞ መዝሙር መቼም ቢሆን አልረሳትም ። ትዝም ትለኛለች ። "አቤት ቆሻሻ ፣ አቤት ቆሻሻ ፣ አቤት ቆሻሻ " አቤት . . .እንደ አጋጣሚ ሆኖ ወጉ ደርሶኝ ቃሊቲን በጎበኘሁ ጊዜም ይህችን "ቆሻሻ " የምትባለውን ቃል በተደጋጋሚ የሚጠሩበትን ሰዎች አይቻቸውም ነበር ። እነዚህም " ቆሻሻ " ተብለው የሚጠሩ ሰዎች በግረሰዶማዊነት ተይዘው የተፈረደባቸው ሰዎች ናቸው ።" ቆሻሾቹ " ማደሪያቸው ሽንት ቤት ፤ መዋያቸው የቆሻሻ ገንዳ ስር ነበር ። ይህን ሁኔታ መንግስት አዝዞ በወንጀላቸው እንዲቀጡ የወሰመባቸው ሳይሆን እስረኛው በራሱ ህግ አውጥቶ ድርጊቱን መፀየፉንና በኢትዮጵያም የተጠላና ሥፍራ የማይሰጠው መሆኑን ማሳየቱና ማረጋገጡም ነው ። 


እነዚህን በቃሊቲ " ቆሻሾች " ተብለው የሚጠሩትን መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ "ቀላጮች " እያለ ይጠራቸዋል ። " . . . አመንዝሮች ወይም ቀላጮች ወይም ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ" 1ኛ ቆሮ 6፣9 ይሁንና ዓለም በተባለች በሰፊዋ ስታዲየም ዛሬ ዛሬ ደግሞ የሚገራርሙ ነውረኞችና ቆሻሻ ድርጊት ፈጻሚዎች ከሚገባው በላይ ቁጥራቸው እጅጉን ከፍ ብሎ በመታየት ላይ ነው ። በተለይ በሀገራችን በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ ይህ አስያፊ ድርጊት እጅግ በረቀቀ መንገድ እንዲስፋፋ እየተደረገ መሆኑን ማሳያ የሚሆኑ ዋቢዎችን መጥቀስ ይቸላል ። ድርጊቱን አስከፊ የሚያደርገው ደግሞ የድርጊቱ ፈጻሚዎች በተለየ ሁኔታ ለዚህ ቆሻሻ ተግባር የሚመለምሉት ጨቅላ ህጻናትን መሆኑ ነው ። በተለይ እንደ አባት የሚታይ መምህር ለትምህርት የላካችሁትን ጨቅላ ልጃችሁን ሲጫወትበት መስማት ይዘገንናል ። ባለፈው ሰሞን አንድ መምህር ይህን ቆሻሻ ተግባር በህጻናት ልጆች ላይ ፈጽሞ በመገኘቱ በፍርድቤት የነበረውን ክርክር ላየ ድርጊቱ ወደፊት ከባድ እየሆነ ለመምጣቱ ምልክትም ነው ። የአውራ አምባው ዳዊት ከበደ በፌስቡክ ገጹ ላይ በግልጽ ይህ አስፀያፊና ቆሻሻ ተግባር በውቢቷ ሀዋሳ ከተማ በግልጽ በተከፈተ የመዝናኛ ክለብ ውስጥ ለውጭ ሀገርና ለሀገር ውስጥ ቆሻሾች ህጻናትን እንደሚቀርቡና እንደሚቸበቸቡ የክለቡን ስም ጠቅሶ መዘገቡን ስናይ በጣም ያስፈራል ። ይህ ድርጊት ሲፈጸም የአካባቢው መስተዳድር አያወቀውም ለማለት አይደፈርም ።"ቆሻሻው" በንጽህትና ቅድስት በሆነችው ክርስትና ስም ሲሆን ደግሞ በእጅጉ ያማል ። ዓለም ወደ ፍጻሜዋ ለማምራቷም በገሀድ ማሳያም ነው ። ቆሻሻው ። ጌታም ስለዚህ ነገር በወንጌል እንዲህ ብሎን ነበር ። " እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥" ማቴ 24፣15 አሁን አሁን የዚህ ዓለም ገዢ የተባለ ዲያብሎስ እጅግ የተለየ ክብር ተሰጥቶት በመላው ዓለም የመመለኪያ መቅደስ እየተሠራለት ፣ የአምልኮ ስርዓቱን አስፈጻሚ የሆኑ አገልጋይ ካህናትና ዘማሪያንም እየተመለመሉለት ፣ የሰይጣን አምላኪዎችም በየአደባባዩ ያለ ሀፍረት በኩራት ደረታቸውን ነፍተው አፋቸውንም ከፍተው የሚመሰክሩበት ዘመን መጥቶላቸዋል። እንዲያውም ለብዙ ዘመናት ሰይጣን ዲያብሎስ ግፍ እንደተፈጸመበት እየተንቀጠቀጡ በእልህ የሚከራከሩለት ትውልዶች ተፈጥረዋል ። እንዲህ የሚሉ ። ሎቱ ስብሀት " . . . በምን እንደሆነ ለማስረዳት አቅም ቢያጡም ፤ ዲያብሎስ እግዚአብሔርን ስለሚበልጠው ፣ ሚካኤልና ገብርኤል ፣ እንደገናም 99ኙ ነገደ መላእክት በጋራ ሆነው ዋና አለቃቸው የነበረን ዲያብሎስን ተዋግተው በግፍ አሸንፈው ከክብሩ አውርደውታል ። መፈንቅለ ሥልጣን በመፈጸም በግፍ ስላባረሩት እኛም የእሱን ክብር በማስመለስ በዲያብሎስ ላይ የተሠራበትንም ግፍ እንበቀልለታለን ይላሉ የሰይጣኒዝም መስራቾቹ ።"አቤት ቆሻሻ. . . እነዚህ የዲያብሎስ አምላኪዎች ለዲያብሎስ የአምልኮ ስፍራ በማዘጋጀት ብቻ አልተወሰኑም ። ከዚያም በዘለል በእምነት ነጻነት ሰበብ ግብረ ሰዶማዊነት መከበር ያለበት መብት ነው በማለት በየ ሀገራቱ ህገመንግስት ውስጥ አንቀጽ ተጠቅሶለት ወንድ ከወንድ ሴትም ከሴት ጋር መጋባት ይችላሉ የሚል አዋጅ አውጀው ህግም አውጥተው በሥራ ላይ እንዲውል አድርገውታል ። 


እንዲያውም ምእራባውያኑ ወደፊት የትኛውም ደሀ ሀገር ይህንን የግብረ ሰዶማውያን መብት አክብረው በህገመንግስታቸው ውስጥ የማያስገቡ ከሆነ ሀገራቱ ምንም አይነት ርዳታ እንደማያገኙ በግልጽ ተናግረዋል ። ይህ ማለት ራበኝ ላለ ሀገር ሰዶማዊ ካልሆንክ ዳቦ አልሰጥህም እንደማለት ነው ። ሰሞኑን ደግሞ ጆሮ አልሰማ አይል ከወደ አሜሪካ ሌላ ጉድ እየተሰማ ነው ። ቀደም ሲል ካኒያ ዌስት አሁን ደግሞ ታዋቂዋ አዝማሪ ቢዮንሴ የአሜሪካንን ህገ መንግስታዊ መብቷን ተጠቅማ በስሟ ቤተአምልኮ መክፈቷን ፣ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ያለ መጽሐፍም ማጻፏን ፣ በቤተ አምልኮው መጥተው በፎቶዋ ሥር ተደፍተው በስሟ የሚማጸኑ ምእመናንን ማፍራቷንም አሰምተውናል፣ አሳይተውናልም ። እንዲያውም ሥዕለ መድኃኔዓለምን በራሷ ምስል ለውጣ ለአደባባይ ማብቃቷም የሰሞኑ ዓብይ ዜና ሆኗል ። " አቤት ቆሻሻ ይሏል ይሄኔ ነው ። . . .ከወደ ደቡብ አፍሪካም በክርስትናና በክርስቶስ ስም በከፈተው አዳራሽ ውስጥ አንድ ወጠጤ ፓስተር የሚሠራውን አሳጥቶት በምእመናኑ ነፍስ የጫወታል ። አንዴ እንደ ከብት ሳር ያስግጣቸዋል ። እባብ ከነነፍሱ ያስውጣቸዋል ። ጸጉር ያስበላቸዋል ። በአፋቸው ውስጥ ከብሪት ጭሮ እሳት ያነድባቸዋል ። ሌላ ጊዜ ደግሞ እንደ ፈረስና በቅሎም ይጋልባቸዋል ። እንደ ፍራሽ በላያቸው ላይ ይዘላል ። እንደው በአጠቃላይ የሚያደርገውን ነው የሚያሳጠዋል ። ህዝቡም አሜን ሃሌ ሉያ ከማለትና የታዘዙትን ቆሻሻ ነገር ከመፈጸም በቀር አንዳች የተቃውሞ ምልክት አያሰሙም ። 


አንዱ ፓስተር የወንድ ፈሳሽ ዘሩን ቅዱስ ወተት እያለ በአዳራሽ ውስጥ ከሰበሰባቸው ሴቶች መሃል መርጦ በግልፅ እየጋተ ያጠጣል ። ሌላው የጴንጤ ፓስተር ደግሞ መንታ መንታውን እንድትወልዱ ብልታችሁን እንድስም ታዝዣለሁ በማለት ከውቅያኖስ ዳርቻ ሴቶችን እርቃናቸውን አስጎንብሶ የርኩሰት ሥራውን በጌታ ስም በአደባባይ ይፈጽማል። ያለጡት ማስያዣና ያለ ፓንት የአምልኮ ስፍራ እንድትመጡ ከሚሉ ፓስተሮች አንስቶ በጌታ ፊት ራቁታችሁን እንድትቆሙ ታዛችኋል በማለት በሰንበት ቸርች ብለው የሄዱ ምእመናንን መለመላቸውን ርቃናቸውን ለሰዓታት እንዲቆሙ ማስደረግ የፕሮቴስታንቱ የዕለት ከዕለት አስነዋሪ ሥራ ሆኗል ። የሚገርመው ምእመናኑን ልብስ አስወልቆ ፓስተሩ ከነ ልብሱ ቆሞ መስበኩ ነው ። "አቤት ቆሻሻ . . .ያልሆኑትን መሆንና ወደ ላይ መንጠራራት የመናፍቃኑ ዋነኛ መገለጫ ባህሪያቸው መሆኑ ይሄ ሁሉ ማሳያ ነው ። አማላጅ አያስፈልገንም ብለው ራሳቸውን አማላጅ የሚያደርጉ ፣ ስግደት ለቅዱሳን አያስፈልግም ብለው መልሰው እነሱ ራሳቸውን የክርስቶስ እንደራሴ ያደረጉ ጫማቸው ስር የሚያስደፉ ሺዎች ናቸው ።እንዲያው በአጭሩ ተቀጩ እንጂ አንድ ሰሞን የእኛዎቹ ሚጢጢ ግሪሳዎችም በድፍረት " ሚካኤልን ራሱ በፍርድ ቀን እኔ አማልደዋለሁ " " ለማርያም አንድ ዝማሬ ብቻ ይበቃታል " ወዘተ የሚሉ ወጠጤዎች ብቅ ብለው ነበር ። " አቤት ቆሻሻ . . .የእኛዎቹ ግሪሳዎች እንደ ቢዮንሴ በድፍረት " ኢየሱስን "መስለው ለመቅረብ፤ የአምልኮ ቤትም ለመክፈት አቅምና ገንዘብ ቢያጡም ቢያንስ በባዶ ቤት " ከመቶ ዓመት በኋላ በዳግማዊ የጋብቻ ሥነ ስርዓታቸው ላይ ዳግማዊ አጼ ምኒልክን ለመምሰል እነ ሀ ገደሉ የበግ ዋሻው የንጉሡን ሻሽና ባርኔጣ በመልበስ መከራቸውን ሲበሉ ማየታችን አልቀረም ። " አቤት ቆሻሻ " . . .


በሌላ በኩልም በአሜሪካው ሲኖዶስ በኩል ብዙ ቆሻሻ ፍልስፍናዎችን ወደቤተክርስቲያን በማስገባት የዋሁን ምእመን ወደ መበከል የሚያመሩ ግልጽ ምልክቶች እየታዩ ነው ። በተለይ አግብተው የፈቱ ደግምው ያገቡም ካህን እያደረጉ ነው ። ፓስተር ሆነው ቆይተው አሁን ለሌላ ተልእኮ " ተመለስን " የሚሉትንም ክህነት እየሰጡ ዳግም ለሌላ ጥፋት ሹመት እየሰጡዋቸው ነው ። በአሜሪካ እነ ኦርጋን ፣ እነ ጊታር ከናይት ክለብ ወደ ቤተ መቅደስ እየፈለሱ ነው ። በታቦቱና በካህናቱ ፊት ሴቶቹ ተገላልጠው ጡታቸውን እያሳዩ ያለ ቅዱስ ቁርባን አንገታቸው ላይ ማኅተብ ሳይኖር ጋብቻም እየፈጸሙ ነው ። ለምስጢር መፈጸሚያም ወይኑን ከሱፐር ማርኬት እየገዙ ነው ። ሴቶችን ገባ ብላችሁ አጽዱ በማለት ከመንበሩ ስር እያስገቡ ደፋር እያደረጉ ነው ። ያለምንም የጸሎት ዝግጅት በድንገት ለቅዳሴ የሄዱትን ምእመናን ታቦት እናውጣላችሁ እንዴ ? በማለት እያላገጡ ነው።" አቤት ቆሻሻ " . . .
ነገ ምናልባትም ግብረ ሰዶማውያን እንጋባ ብለው ቢመጡ " ምን አለበት " ደግሞም " ዚስ ኢዝ አሜሪካ " ወዘተ እያሉ ላለማጋባታቸው ምንም ዋስትና የለንም ። በዚያ ያላችሁ አባቶች ይህን መሰሉን ድርጊት ተጸየፉት ። አለመተባበራችሁንም አሳዩን ።


በመጨረሻም ለመናገር የምፈልገው ነገር ቢኖር እንደሚከተለው ነው ። ድምጼን ከፍ አድርጌ ክብር ለአባቶቼ ይሁን እላለሁ ። ከራሳቸው ይልቅ መስቀሉን ፣ ታቦቱን ፣ መቅደሱን ፣ ቅዱሳት ሥዕላቱን እንድንፈራ ፣ እንድናከብር ላደረጉን ። የጌታን አምላክነት ፣ የቅዱሳንን አማላጅነት ነግረው ፣ ሰብከው ፣ ጽፈውና ደጉሰው ላስቀመጡልን አባቶቻችን ይሁንልን ። ይህን ድርጊት እግዚአብሔር ከሚጸየፋቸው ድርጊቶች ዋነኛው ኃጢአት ነው ። እሳትና ዲን ከሰማይ የዘነበበት ፣ ሰዶምና ገሞራ የጠፉበት ፣ ወደ አመድነትም የተቀየሩበት ተግባር ነው ። እስቲ በግልጽ እናውራ ፣ እንወያይም ። ሁላችንም ቆሻሻውን ለማጽዳት ፣ ሀገራችንንም ከዚህ ነውረኛ ድርጊት እንጠብቅ ፣ በአካባቢያችን ፣ በሰፈራችን ያሉትን ቆሻሾች እግዚአብሔር ወደ ልቦናቸው ይመልስልን። " እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥" ማቴ 24፣15።

                                              ምንጭ፦Zemedkun Bekele
                                              መጋቢት 4/2008ዓ ም

No comments:

Post a Comment