Sunday, May 15, 2016

ለአንቺ


ባህር ወደታች ምን ያህል ጥልቅ ነውዓለምስ ወደጎን ምን ያህል ይሰፋልፀሐይ ምን ያህል ትርቃለችከዋክብት ምንኛ ይበዛሉየሰው ልጅ ልቦና ምን ያህል ርቀት ይመሰጣልአእምሮው እስከየቱ ጥግ እስከምን አጥናፍ ድረስ ያስባልሁሉም ወሰን አለው። ሁሉም ዳር ድንበር ጥግ አለው።ምድር ምንም ፍጹም ነገርን እንደማታስተናግድ ትባላለች። ፍጽምና የለባትም ይባላል። ሁሉም ጎዶሎ እንደሆነ ይነገራል። ሁሉም ሙሉ ለመሆን አንዳች ሌላ ግብዓት ይሻል። ቀን ያለፀሐይ፤ ምሽት ያለ ጨረቃና ከዋክብት፤ ዝናብ ያለደመና፤ ደስታ ያለመከራ፤ ድል ያለውጊያ አይገኙም። ዓለም ራሷ ምኗም ሙሉ አይደለም። አንዱ ከአንዱ ጋር ይደጋገፋል።ትዕግስት ጠረፍ አለው፤ ጽናት ገደብ አለው፤ ሸክም ልክ አለው። የሰው ልጅ «ከዚህ በላይ አልችልም፤ ከዚህ በላይ አልታገስም፤ ከዚህ በላይ ይከብደኛል» የሚለው ጠርዝ አለው። ይደክማል። ይሰለቻል። ቢታገስ እንኳን ያማርራል፤ ቢጸናም ተስፋው ይዝላል፤ ቢሸከምም ደርሶ አውርዶ ሊጥል ይናፍቃል።ሰው ስልቹ ነው። ሰው ወረተኛ ነው። ዛሬ የያዘው ወርቅ ነገ መዳብ ይመስለዋል። ዛሬ ያመሰገነውን ነገ ሊኮንነው ይችላል፤ አሁን ለሳቀለት አፍታም ሳይቆይ ይነክሰዋል። ሰው ወረተኛ ብቻ አይደለም። ደግሞም ራሱን ወዳድ ነው። ለእርሱ እንደተመቸው ብቻ፤ ለእርሱ እስከሆነለት ብቻ ነው ምንም ነገር ቢሆን የሚፈልገው።

እንዴእኔ ሰው አይደለሁ እንዴከባህር ጥልቀት በጠለቀ፣ ከዓለም ስፋት በሰፋ፣ ከፀሐይ ርቀት በመጠቀ፣ ከከዋክብት ቁጥር በበለጠ፣ ልቦናዬ ከሚያሰላስለው አእምሮዬ ከሚያስበው በላይ፤ እስከማላውቀው ጥግ፤ እስከማይታየኝ ድንበር፣ ይህ ነው እስከማይሉት ወሰን የምወድሽ ስለምን ነው?እንዴአንቺስ ሰው አይደለሽ እንዴፍጽምናሽ ከየት መጣብቻሽን ሙሉ ነሽ። ሌላ ምን ያሻሽናሲጠሩሽ ጥግብ ይላሉ፤ ሲያስቡሽ ፈገግታን ደስታን ያገኛሉ፤ አንቺ አይደለሽምስምሽ ራሱ ሙሉ ነው። ቅጥያ ቢሰጡት፤ «...ዬ »ን ጨምረው ቢያቆላምጡት ምኑም ነው።እንዴሰው አይደለሽ እንዴጥግ የሌለው ትዕግስት፣ የተሠራሽበት የሚመስል ጽናት፣ የማይሰለች የማይታክት ትከሻ። ምንድን ነውደከመኝ አላልሽ፤ ሰለቸኝ አታውቂ። ትዕግስትሽ ምሬት የሌለው፣ ጽናትሽ ተስፋው ያልተነካ፣ ትከሻሽ ምንም የሚከብደው የማይመስል። ከምን ተሠርተሽ ነውከማን ወጥተሽ ነው?እንዴሰው አይደለሽ እንዴምነው ወረት የማታውቂአርባ ዓመት ሃምሳ ዓመት የዕድሜሽን እኩሌታ መንከባከብ፣ መንሰፍሰፍ፣ መጨነቅ አይሰለችሽም። ምን ያለ ልብ ነው ቆይ ዋንጫም ይዞ ቢሄድ ተሸነፍኩ ብሎም ቢያለቅስ እኩል አቅፎ የሚቀበል። ትናንት የተጨበጨበለትን ዛሬም የገፉትን ሰው ያለአንዳች ልዩነት የሚያቅፍ ክንድ ምን ያለ ነው።አሰብኩትያኔ መነሻሽን መምጫሽን አየሁት። ከማትሰለች ማህጸን፤ እኔን ከምትል እንስፍስፍ ገራገር፤ ምኞት ምርቃቷ ለሰው ልጅ ሁሉ ከተሰጠው ልብ ሳይሆን ከሌላ ለየት ያለ፤ ለብቻዋ የተፈጠረላት ከሚመስል አካል የሚወጣ፤ ውሳጣዊ የሆነ። የማይበረታ አንድ ነገሯ ቁጣዋ ብቻሰው ናት እንዴ!?ሰው ነሽ እንዴአልኩኝ። 

አዎን ሰው ናት ለካ
ግን ትለያለች፤ እንደሰው ከሚደክም፣ እንደሰው ከሚታክት፣ እንደሰው ከሚሰለች ባህርያት ተፈጥራለች ግን እንጃ ፈጣሪ አንዳች ነገር ሳያክልባት አልቀርም፤ ትለያለች። የዓለም ነገር ያለእርሷ ምን ነበርያለእርሷ እንኳን ወጥና ዓለምስ መች ይጣፍጥ ነበር። ያለእርሷ እንኳን አንድ ሰውና ሕዝበ አዳም ሁሉ መች ይጽናና ነበር።አየሽ የፍቅርሽን ጥልቀት፤ ሰው መሆንሽን ስጠራጠር፤ እኔም ጽንፍ የሌለው ላንቺ ያለሽ ፍቅር ሰው መሆኔን ሲያዘናጋኝ። የእኔ ልብ ለአንቺ እንዲህ ከሆነ የአንቺስ ምንኛ ይበረታእኔ ከምወድሽ በላይ የምትወጂኝ ሆይምን ያለ መውደድ ነው ይሄዓለምስ ሁሉ እንዲህ ያለው ፍቅር እርስ በራሱ ቢታደል ኖሮ ይህቺ እሾሃማ ምድር «ገነትን» በመሰለች አልነበር!ከራስሽ ይልቅ የልጅሽ ህመም ያምሻል፤ ርቀቱ ይጨንቅሻል፤ ድሉ ያስፈነድቅሻል፤ ውጤቱ ያኮራሻል፣ መኖሩ ደስ ያሰኝሻል። ልጅሽ በመኖርሽ የኖረ፤ በመገኘትሽ የተገኘ በምጥሽ የተነፈሰ ነው። ምን አለ የተባለ ፈላስፋ፣ ዓለምን ያስጨበጨበ ጠቢብ፣ ከሁሉ በላይ ነግሶ የታየ ጀግና ለአንቺ ምን አድርጎ እንደሆነ ቢጠይቁት መልሱ ዝምታ ነው።ቅሉ አንቺ አትጠይቂም እንጂአንቺ ይህን አድርጌ ነበር፤ ይህን መልሱልኝ አትይም እንጂያንን ሰርቻለሁ ማለት አታውቂበትም እንጂ ብትይማ ጉድ ፈልቶልሽ ነበር። ለሠራሽው ሥራ፣ ላደረግሽው ሁሉ ምን ይመለስ ነበር?

ያንቺ ሥራ ከውለታ የሚጻፍ አይደለም፤ ስንቱ ጉዳይ፤ ስንቱ ትንሽም ትልቅም ነገር ውለታ እየተባለ ሳለ የአንቺን ነገር እንዴት ውለታ ልበለው። ደግሞም ውለታ የሚመለስ እንጂ የሚተውት አይደለምና። ብቻ ሌላ ወካይ ቃል ስለሌለ ውለታ እንበለውና ያንቺን ውለታኮ የመለሰ የለም። ቢኖርማ ምንኛ በታደልን ነበር። እንዲያው ሁሉም ይዞት ያልፋል። ወርቅና እንቁ የከበረ ድንጋይ እንደምን ሆኖ ለአንቺ ስጦታ ሊሆኑ ይገባቸዋል። ብዛት የሌላቸውና በጥቂቱ የተገኙ መሆናቸው እንጂ እነርሱ ድንጋይ ናቸው። አንቺ ራስሽ
'ኮ ስጦታ ነሽ። ለአንድ ሰው አንዴ የምትሰጪ፤ የማትደገሚ የማትሰለሺ።እናት ሆይ፤ ከየት መጣሽምን ዓይነት ፍጡር ነሽ እልና፤ ደግሞ ሳስብ ጥቂቷ እውቀቴ፤ ትንሿ ማንነቴ ሹክ ትለኛለች፤ አንድ ነገር ብቻ። ለካንስ የወለደችሽ እናት ናት።
አዲስ ዘመን ጋዜጣ
 ግንቦት 8, 2008

No comments:

Post a Comment