የተከበርክ ምላሴ ሆይ፡አርምሞን ገንዘብ አድርግ።አንተም ብዕረ አርምሞ የሚል ቃልን ጽፈህ ልቦናየን ለሚያውከው
ለዓይኔ መልእክት እንዲደርሰው አድርግ።ሥጋየ ፈቃድ በተነሳበት ጊዜ የጌታየን፣የፈጣሪዬን መከራውንና ግርፋቱን አስብ
ዘንድ ልቦናየ ይህን እያሰበ እንዲበረታ እንዲህ ከሆነ ለዓለማዊ ህይዎት ሙት እሆናለሁ።ሣጋዊ ምኞትና ፍላጎት
በነገሰበት ሕይዎት ለ አርባ አቅናት እንደ ጌታ ት ዝዛና ሕግ ልቡናዬን በንጽህና ለመጠበቅ ይቅርታ ለሚያሰጠው
ህይዎት የተገባሁ እንድሆን።የ አባቶችን ምክር እቀበላለሁ፣የቅዱሳንን ፍኖት እከተላለሁ በከንፈሮቼ ላይ መዝጊያን
አኑር ምክን ያቱም ብዙ መማር ስለሚገባኝ ነው የምናገራቸውን ቃላርት እመጥን፣ሰውነቴን ለመቆጣጠር እችል ዘንድ፤
አንደበት የነስን ሩጫ ያሳድፋልና ሞገደኛ በሆነ የጻለ ሾተል ሰዎችን የሚገድል ሰው በቀላሉ ትንሽ ቁጥር ያላቸውን
ሰዎች ያንበረክካል።ክንፍ ያላትን ከወጋች የንማትነቀለውን የምላስ ጦር የወረወረ ሰው(በ አላማም ያለ
አላማም)አላማውን አይስትም።የቀረቡትን ሁሉ ያቆስላል ፤የመረዘውን ሁሉ ይገድላል።በጾም ወራት ሕሌና ፍጹም መረጋጋት ያስፈልገዋል።ከምድራዊ ሃሳቦች ሁሉ የጸዳ ከሰዎች ተለይቶ ብቻውን ከ አምላኩ ጋር የሆነ ሊሆን ይገባል።ሕሊና የኃዘን ደመና ሊያንዣብብበት ይገበዋል። ውጤቱም እርጥበት እንባን የሚያስከትል መራር ኃዘን ነው።
ታላላቅ ነገሮችን ለመቆጣጠር የሚፈልግ ሰው ትንንሽ ነገሮችን መቆጣጠር ይኖርበታል። የምላሴን ኃይል ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ያለብኝ ከንፈሮቸ ምንም አይነት ቃላት እንዳያፈሱ ተስፋ አድርጌ ለሰው ልጆች መርዙ የማይነቀል ገደይ እንደ ምላስ ያለ የለምና ነው። ምላስ ዘወትር ግልቢያን እንደሚናፍቅ ከፊት ለፊት ያለውን ሁሉ ቀድሞ ለማለፍ እንደ ሚጋልብ ፈረስ ነው። ምላስ የተዘጋጀ የተደገነ ቀስት ነው። ሁሉን ማየት የሚቻለው ማን ነው? እጅ በአቅራቢያ የሚገኘውን ትንሽ ነገር በቀላሉ ይጨብጣል ፤እግርም ሁሉንም የመሬት ክፍል አይረግጥም፤አይንም ሰሜንና ደቡብን አይመለከትም፤ምላስ ግን የማይደርስበት ቦታ የለም። ምድርን ሁሉ ያካልላል ለነፍሰ ገዳዮችና ጣኦትን ለሚያመልኩ፣ሐሰትን ለሚዎወዱ አድጋ ነው በእብደታቸው ላይ ሌላ እብደት ይጨምርላቸዋልና። የፈጠነን ምላስ ሊያስቆም የሚችል ምድራዊ ኃይል የለም። ለመናገር የቸኮለ ከንፈርንም እንዲሁ ሰውም ቢሆን ውሽንፍርም ቢሆን፣የበረዶ ግግርም ጎርፍም፣ተራራም ቢሆን ባለ ቀስቱ ቅርብ ነው። ቀስቱ የተደገነ ነው፤ቀስቱ በደጋን ላይ ነው። አንድ ጣቱን ደጋን ላይ አድርጎ አክሮ ቀስቱን ይወረውራል፤በረው የታለመላቸውን አላማ ይመታሉ። ሰማያዊያን ምድራዊያንም ቢሆኑ አያመልጧቸውም። ሕያዋንንም ሙታንንም ያለፉትን የሚኖሩትንና የሚመጡትን ሁሉ ይገድላል። የምላስ ቀስት እንዳይወረወርባቸው የሚጥብቁትንም የማይጠብቁትንም የተጣላቸውንም ወዳጆቹንም አይምርም።