Monday, January 06, 2025

እኔና ዝናዬ ጨክነናል

ወርኃ ጥቅምት 2017 ዓ.ም መንግሥት አድርጌዋለሁ ያለው 300% የደሞዝ ማሻሻያ ተግባራዊ ሊደረግ ነው የሚል ዜና በሰማንበት ማግስት ደጉ አከራያችን ሆስፒታል አድሬ ስመለስ ጠብቀው ያዙኝና " ቁርስ በልተህ ቡና ጠጥተህ ተመልስና የማናግርህ ነገር አለኝ " አሉኝ።  የታዘዝኩትን ፈፅሜ ተመለስኩና ለምን እንደፈለጉኝ ስጠይቃቸው ወቅቱን ያማከልና ከጥቅምት 30/2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን የቤት ኪራይ ማሻሻያ ለማድረግ መወሰናቸውንና ልጅ አሳዳጊ መሆናቸውን፣ የኑሮ ውድነቱም እየናረ መሆኑን ታሳቢ በማድረግ በወር 700 ብር ብቻ እንደጨመሩብኝ አረዱኝ።

በተመሳሳይ ቀን እኔና ዝናዬ በጠረጴዛ ዙሪያ ቁጭ ብለን ከተወያዬን በኋላ ቁርጥ ያለ ውሳኔ ላይ ደረስን። አንበላም አንጠጣም ብለን የገዛናትን  ቤት አዘገጃጅተን ለመግባትና ዶሮ እርባታ ለመጀመር ተስማማን። ውሳኔው ቀላል የሚባል አልነበረም ፤ ጭካኔ ይፈልጋልና ጨክነናል። ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በሯን አስገጥመን፣ ውስጧን አስለስነን፣አጥሯንም በቆርቆሮ አሳጥረን በእለተ ሐሙስ ህዳር 12/2017 ዓ.ም (የህዳር ሚካኤል እለት )እቃችን ጠቅለለን ወደ ቤታችን ገባን። የቤት መግዣውን ሳይጨምር ውስጧን ለማስለሰን 16000 ብር፣በርና መስኮት በላሜራ ለማሰራት 17000 ብር፣ አጥሯን በቆርቆሮ ለማሳጠር 24000 ብር በድምሩ 57000 ብር ጨርሶብናል።

ይህን ለማድረግ ደግሞ ወደፊት የግል ክሊኒክ ለመክፈት የገዛሁትን centrifuge(15000 ብር ), autoclave(15000 ብር ), examination bed(6500 ብር),  ፍሪጅ(25000 ብር ተገዝቶ 18000 ብር የተሸጠ)፣ እንዲሁም ለማንበቢያ የገዛኋትና እንደ ዓይኔ ብሌን የምወዳትን Tablet(9000 ብር) መሸጥ ነበረብኝና ሽጥኩ። መጨከን ነበረብኛ!
ዶሮ እርባታውን ለመጀመር ግን ጨክኖ መነሻ በጀቱን የሚሸፍንልን sponsor እንፈልጋለን።
አስቻይ ሁኔታዎች
1ኛ የተመቻቸና በቂ ቦታ ያለን መሆኑ
2ኛ. ቀዳማዊት እመቤቷ ( ወ/ሮ ዝናሽ መኬ ) የተመሰከረላቸው የዶሮ እርባታ expert መሆናቸው
3ኛ. የጠቅላዩ ዶሮ እርባታን የሚያበረታታ አቋም

በጀት
የቄብ ዶሮ መግዣ: 100*300=30,000
የዶሮ ቤት መስሪያ: 10,000-15,000
የቄብ መኖ 5 ኩንታል*5000ብር =25000
መመገቢያ 4*300= 1200
መጠጫ :2700
የእንቁላል መጣያ ሳጥን: 1500
የእንቁቃል መሰብሰቢያ: 270
አካፋና መዶሻ :2*500=1000
ሳፋ :2*400=800
ፕላስቲክ ባሊ:2*200=400
ለውኃ ማስገቢያ :10,000-15,000
ሮቶ :2000
ለክትባትና መድኃኒቶች(H2O2ና ሳሙናን ጨምሮ) :5000-7000
ሌሎች ወጪዎች 15000-20000

ጠቅላላ ድምር 80000-120000

እኔና ዝናዬ ጨክነናል!
ዝናሽ የዶሮ እርባታ  ማእከል እውን ይሆናል።

19 ዓመት ተምሮ ለምድር ለሰማይ የሚከብድ ማእረግ እንደተጫነበት አንድ ኢትዮጵያዊ ሀኪም ይህን ጦማር ይዞ  ማህበራዊ ሚዲያ ላይ መውጣት በራሱ ሌላ ከፍ ያለ ጭካኔ ይጠይቃል።
ገረማችሁ አይደል። አትገረሙ ደግሞም አትሰስቱ ። ይልቁንም የአቅማችሁን ጠጠር ወርውሩ  ፤ repost በማድረግም ለሚመለከታቸው አጋር አካላት አድረሱልን።
ስልክ:+251918666678/+251962443989
BOA Acct: 212465933
                      ZINAYE MEKIE YITAYH
CBE Acct: 1000316337949
                     Getaneh Kassie Gashu

https://lnkd.in/gjmvvQ4h




No comments:

Post a Comment