Sunday, October 15, 2017

ታላቅ የምስራች

ታላቅ  የምስራች ለደስታዬ ተካፋዮች በሙሉ እነሆ ያኔ ገና  በልጅነት እድሜ በግ እና ፍየሎችን እየጠበቅሁ ያኸለምሁት ህልሜ  እውን መሆኑን  ምክንያት በማድረግ ከዛሬ ጀምሮ ብሸከም የማልችለውን  ማዕረግ ከፊት በማስቀደም ዶ/ር  ጌታነህ ካሴ ተብዬ እንድጠራ የተፈቀደልኝ መሆኑን ስገልጽላችሁ በታላቅ ደስታ  ነው። ዘወትር  ከጎኔ ሁናችሁ አይዞህ እያላችሁ ለዚህ ታላቅ ክብር እንድበቃ ላደረጋችሁኝ ወንድሞቼና እህቶቼ በሙሉ ውለታችሁን ከፍየ አልጨርሰውምና  እግዚአብሔር ዋጋችሁን  እጥፍ ድርብ አድርጎ ይክፈላችሁ  እላለሁ። እውነት ለመናገር በዚህ ሰው አምላኩን ረስቶ  ገንዘቡን ማምለክ በጀመረበት ዘመን “መወለድ ቋንቋ ነው” የሚለውን ብሂል በተግባር ያሳያችሁኝ ለእኔ የተሰራችሁ የፍቅር ጣኦታት  ናችሁና ሳመሰግናችሁ ውየ ሳመሰግናችሁ ባድር አይወጣልኝም። ተምሮ ሰው ይሆንልኛል በሚል ተስፋ ከእለት ጉርሳችሁ ይልቅ ለእኔ በማድላት ላስተማራችሁኝና ጠንቅራችሁ ብርታት ለሆናችሁኝ ቤተሰቦቼ ደስ ብሎኛልና ደስ ይበላችሁ እላለሁ። በቸርነቱ ብዛት ለዚህ ያበቃኝ አምላክ ከእናቱና ከቅዱሳኑ  ሁሉ ጋር ክብርና ምስጋና ይድረሰው። አቤቱ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ  የልመናየን ቃል ሰምተኸኛል እና  አመሰግንሃለሁ። ድንግል ሆይ አንቺ የጽርሐዓርያም ብርሃን ከጎኔ ሆነሽ ታረጋጊኝና ግርማ ሞገሥ ትሆኝኝ ዘንድ እኔ ማን ነኝ
      መች ተነግሮ ያልቃል ያምላክ ቸርነቱ
እኛስ ብለን ነበር ቀረን ሆነን ከንቱ
በፍፁም ትሕትና አሃዱ ቢል ቄሱ
በመልካም ውብ ዜማ ስሉስ ቢቀደሱ
መንቨሩ ፊት  ብትቆም ደጓ የዓለም ቤዛ
አምላክም በፋንታው ምህረቱን  አበዛ
በሃያል ስልጣኑ ጥልን  ደመሰሰ
ያጣነው ልጅነት ዳግም ተመለሰ
መለያየት  ቀረ ውላችን ታደሰ
እረኞች ዘመሩ ፍጥረት ተደመመ
በህይወት  አዳራሽ  ማህሌት ተቆመ
Dr. Getaneh Kassie

No comments:

Post a Comment