Love joy and peace are deep state of being..........as such they have no opposite. This is because they arise from beyond the mind. Accordingly real love doesn't make you suffer. How could it ? It doesn't suddenly turn into hate,nor does real joy turn into pain .
The reason why many love relationships after the initial euphoria passes,or oscillate between "love" and hate,attraction and attack, is that what we usually call love is the short lived pleasurable aspect of emotion which is subject to the law of opposites; which states every thing that gives you pleasure today will give you pain tomorrow,or it will leave you,its absence will give you pain. . . . . . {the power of now}
ከዩኒቨርሲቲ መመረቅን ምክንያት በማድረግ “ስለነበረን ጊዜ አመሰግናለሁ።” የሚል መልእክት ((መርዶ)) የደረሳችሁ ወይም ለመባል በዝግጅት ላይ ያላችሁ “አፍቃሪያን” መፅናናትን ከአርያም ይልክላችሁ ዘንድ እመኝላችኋለሁ።አንዳንዶች የገንዘብና የዝሙት ጥማታቸውን አወንታዊ ገጽታ በተላበሰ መልኩ ለማርገብ ሲፈልጉ “ፍቅር” የሚል ስም ይሰጡታል። ታዲያ ይህን ድብቅ ጥማታቸውን የሚያስታግስ የተሻለ አማራጭ ሲያገኙ የቀደመ ፍቅራቸው በጥላቻ፣ መውደዳቸውም በንቀትና በኩራት ይተካል።
እውነተኛ ፍቅር ግን እየተጠሉ መውደድ፤እየተካዱም ማመን ነው። እውነተኛ ፍቅር ይታገሳል ፤ ቸርነትንም ያደርጋል እንጂ አይቀናም ፤አይታበይም ፤የማይገባውን አያደርግም ፤በደልን አይቆጥርም። እውነተኛ ፍቅር ማለት የሚወዱትን ሰው አስገድዶ የራስ ማድረግ ወይም የራስን ፈቃድ ማስፈፀም ሳይሆን የተወዳጁንም ምርጫና ፍላጎት ማክበር ነው።
ሳንጠይቀው ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ የፈጠረንና አንድያ ልጁን ለሞት አሳልፎ እስኪሰጥ ድረስ እንዲሁ የወደደን እግዚአብሔር እንኳን “እኔ የፈጠርሁትን አየርና ውኃ፣ ፀሐይና መሬት እየተጠቀማችሁ፤ የበደላችሁንም ካሳ ከፍዬ ከኀጢአት ባርነት ነጻ አውጥቻችሁ፤ እኔን ከመውደድ (ከማምለክ) ውጪ ሌላ አማራጭ የላችሁም” አላለንም። የእውነተኛ ፍቅር መገለጫው ይህ አይደለምና። ((©ጌች ቀጭኑ))