Sunday, May 17, 2020

"We need our limited health resources for things which are actually killing us"

We are chasing COVID 19 off a cliff.
The majority of our population, who don't already seek modern medical care are now even more afraid to visit hospitals. For this reason work at hospitals has slowed down.

Health education given about COVID 19 doesn't seem balanced based. Based on the world population review, in our country 1984 peoples die every day and a big chunk of that number is by medical reason. Remember why we let RVI +ve mothers to breast feed, inspite of clear CDC recommendation that "the best way to prevent MTCT through breast milk is not to breastfeed" We  rather take the risk with the RVI than the malnutrition. We should apply the same principles in this scenario.

Let me refer the EDHS 2016 and mention the areas which will be affected more by the decreased patient flow. In Ethiopia, 73% births occur at home with a high maternal mortality rate of 412/100,000 live births and  81 % don't recieve any  postnatal care. "According to Health data .org neonatal disorders are the number one causes of death in Ethiopia". Back to EDHS, the basic vaccination coverage for all eight basic vaccines is 40 % .

You know there isn't much recent data about our morbidities but let's take a report by "world life expectancy" to have a general picture. Diarrheal diseases account for 8% of deaths in Ethiopia, 3.81% are due to Tuberculosis, 7.38% are due to Coronary Heart disease, 3.21 l are due to HIV, stroke 6.23% , cirrhosis 2.24% and meningitis 2.8%. If we consider the world population review report of 1984 death per day in Ethiopia. We will have rough estimation of our disease burden.
©Dr.Kirubel Tesfaye

Tuesday, May 05, 2020

አላቲኖስ



የፊስአልጎስ ሕቡዕ  የመሰብሰቢያ አዳራሽ በዝምታ አርምሞ ተመቷል።ብዙዎች የገመዳ ውሳኔ ያልጠበቁት የማይታመን ሆኖባቸዋል ።ገመዳ ብዙ ሰላማያወራ ብዙም ስለማንነቱ እንዳያውቁ ስላደረጋቸው መደነቅን ፈጥሮባቸዋል ።

የመሰብሰቢያ አዳራሹን ፀጥታ “አይሆንም”የሚለው የታንቱ ንግግር አደፈረሰው ።”…ይህማ አይሆንም ምን ማለት ነው ?ለምንድነው ለልጆችህ ሰቀቀን የምትሆነው ?ስለምንድነው ይህን የሚያክል ሃላፊነት ትተህ ራስህን ለመከራ የምትዳርገው ?ባይሆን እኔ ሕይወትን ያልጀመርኩት ሐላፊነቱን እወስዳለሁ እንጅ እንዴት ነው አንተ የምትማገደው?”አለ ታንቱ እንባ እየተናነቀው ።

ሐዊ ክው ብላ ደንግጣለች ።ስለደነገጠች ነው መሰል ጉንጯ መሰርጎዱን ያቆመ ይመስላል።በታንቱና በገመዳ ፍቅር ፤ከምንም በላይ ለቤተ ክርስቲያን ሕይወታቸውን ለመስጠት ያላቸውን ቁርጠኝነት ስታይ ደነገጠች ።ክርስትና ከዚህም  በላይ ዋጋ እንደሚያስከፍል በታሪክ ከቅዱሳን መጽሐፍት ብታነብም እንዲህ በዓይኗ ግን ‘እኔ ልሰዋ እኔ ልሰዋ ‘ሲባል አላየችም አልሰማችም።

አበጋዝም ይህ ፍቅር አስደግጦታል።ሌሎች የሥራ አስፈጻሚ አባላትም  የሚናገሩትን ቃላት አጡ።አብጋዝ ግን እንደ ምንም ልውጣ አልውጣ የሚለውን እንባውን አምቆ መናገር ጀመረ ።”እናንተ ምን በወጣችሁ ነው ዋጋ የምትከፍሉት ያወራሁት እኔ ፤የሰበክሁት እኔ፤የደሰኮርኩት እኔ፤ እንዴት ተደርጎ ነው እኔ እያለሁ እናንትነ ሃላፊነት የምትወስዱት ?”

“አይሆንም”አለ ታንቱ በድጋሜ።ሁሌም እንደሚያደርገው መሃል አናቱን ቆፈር ቆፈር አደረገና”አይሆንም ምክንያቱም ብዙ ሰዎች አንተን የማህበረ ቅዱሳን አባል ነው የሚያድርጉህ፤ ስለዚህ አንተ እኔ ነኝ ብትል ለማህበሩ ሌላ መከራ ትጠራለህ እንጅ የምታመጣው ለውጥ የለም።ትርጉም የለሽ መስዋዕትነት ደግሞ አንከፍልም ።የምንከፍለው መስዋዕትነት ደግሞ በምድርም በሰማይም በረከት ቢያመጣልን መልካም ነው ።ሲቀጥል ትናንት አውደምህረት ላይ ሰብከህ ዛሬ ገዳይ ብትባል አሁንም ለቤተክርስቲያናችን ውርደት ነው ።እኛ የማንታወቀው ግን ምንም ችግር የለውም ።”የመሰብሰቢያ ክፍሉ ለጥቂት ሰከንድ ፀጥ አለ።

ዝምታውን ለመስበር ያህል ገመዳ ንግግሩን ዳግም ጀመረ ።”ሁላችንም መስዋዕትነት ለመክፈል የሚያስቸኩለን አይመስለኝም።ዘመኑ ዋጋ ይጥይቃል ስለዚህ ብንቀዳደም እንጅ መስዋዕትነቱ እንደሆነ ለእያንዳንዳችሁ አይቀርላችሁም። ስለዚህ እንደፊስአልጎስ ሰብሳቢነትም ቅድሚያ ሐላፊነቱን ልወስድ ግድ ነው ።ከከራድዮን ወፍ የምንማረው ይህንኑ ነው ።በዚያ ላይ ናፍያድን አውቀዋለሁ።ዩኒቨርሲቲ በአንድ ወቅት ተምረናል።አንድ ዶርምም ኖረናል ስለዚህ ምን አገናኝቷቸው ገደለው ለሚለው ጥያቄ መልስ ይሰጣል።ስለዚህ ይህን ጉዳይ በዚህ እንዝጋውና ስለቀጣዩ ነገር እንወያይ።

ይልቁንስ እኔ ዛሬ የጀመርኩትን ሰማዕትነት እናንተም ቀጥሉበት ።ይህን ሰማዕትነት አላቲኖስ ብየዋለሁ።አላቲኖስ ማለት እውነት፣ከማናቸው በላይ ንጹሕ ማለት ነው ።ለቅድስት ቤት ክርስቲያን የምንከፍለው ዋጋ ንጹሕና እውነት ብቻ ይሆናል።ስለዚህ ሰማዕተ አላቲኖስን ጀመርኩት እንጅ የምትጨርሱት እናንተ ናችሁ።”ሁሉም ስለገመዳ ጽናትና ቆራጥነት ተገረሙ።

አበጋዝ  ደግሞ ‘ይህቺ ቤተክርስቲያን ዛሬም ልጅ አላት ፤ ቅዱስ ያሬድን፣ ላሊበላን፣ይምርሃነ ክርስቶስን፣አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫን፣አባ ቀውጦስ፣አባ ፊሊጶስ፣አቡነ ጴጥሮስን ፣አቡነ ቴዎፍሎስን ፣መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬን፣…የሚተካ ልጅ ዛሬም ተወልዷል ።’እያለ ለራሱ ሲደሰኩር ነበር ታንቱ ንግግር የጀመረው ።

በዚህ የወረርሽኝ ሰዓት ሁሉም ሰው በተለይም ‘ክርስቲያን ነኝ’ የሚል ሁሉ ሊያነበው የሚገባ ሌላ ድንቅ መጽሐፍ ።
Stay at home till the pandemic is over
Keep calm read books with red cover
 አላቲኖስ

አርበኝነት

ሳሎን ላይ ነው እንጅ
ቤትን ጥርቅም አ'ርጎ ከርችሞ በመዝጊያ
ምሽግ ውስጥ አይደለም ያንተና እኔ ውጊያ
በማዳን ነው እንጅ በማፅዳት እጃችን
በመግደል አይደለም አርበኝነታችን
.
መልካም የአርበኞች ቀን

ዶ/ር በላቸው ደስታ


(Legendary Ethiopian Pharmacist)








በኢትዮጵያ የዘመናዊ የፋርማሲ አልግሎት ታሪክ ስማቸው ጎልቶ ይነሳል።የተወለዱት ዳንግላ ነው። ከአባታቸው ከአለቃ ደስታ ድንበሩ እና ከእናታቸው ከወ/ወሮ ህልሚቱ ኪዳኑ ነሐሴ 03፣ በ1935 ዓ.ም ተወለዱ። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን እዛው ዳንግላና ቻግኒ ተማሩ። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ጄኔራል ዊንጌት ተቀላቀሉ።

በቀዳማዊ ኃ/ስላሴ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገሪቱ ከተመረቁ ሶስት የፋርማሲ ባለሙያዎች አንዱ ናቸው። የማህበረሰብ ፋርማሲና የኢትዮጵያ መድሃኒት ፋብሪካ ሰርተዋል። ወደ ቫንኮቨር ካናዳ አቅንተው በብሪቲሽ ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የማስተርስና የፒኤችዲ ትምህርታቸውን አጠናቀዋል።

 የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፋርማሲ ት/ቤት ዲን ሆነው ለ9 ዓመት አካባቢ አገልግለዋል። በተቋሙ በቆዩበት ዘመን ተባባሪ ፕሮፌሰር በመሆን በርካታ ጥናቶችን አበርክተዋል። ለረጅም ዓመታት የዘለቀውን የ5 ዓመት የፋርማሲ ስርዓተ ትምህርት በመቅረፅ፣ ት/ቤቱን በአቅምና በትምህርት መሳሪያ በማደራጀት፣ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ፈንድ በማምጣት ትልቅ አስተዋፅኦ አድርገዋል።

 አንጋፋውን የኢትዮጵያ ፋርማሲ ማህበርን ከመሰረቱት ውስጥ አንዱ ናቸው። የማህበሩ የመጀመሪያው ፕሬዘዳንትም ናቸው። በጤና ጥበቃ ሚንስትር የፋርማሲ ዲፓርትመንትን በመመስረት፤ የአሁኑን የኢትዮጵያ የመድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲን (በቀድሞ ስሙ "EPHARMAECOR") በመመስረት ሂደት ውስጥ ትልቅ አስተዋጽኦ ነበራቸው። የሶስት ልጆች አባት የሆኑት ዶ/ር በላቸው ደስታ የጡረታ ዘመናቸውን በባህላዊ ህክምና ላይ ጥናት በማድረግና እራሳቸውን በመደገፍ ነበሩ። በዚህ ዘርፍ እየሰሩት የነበረ ጅምር ስራ እጃቸው ላይ እንደነበር ሰምቻለሁ። ታመው ግሩም ሆስፒታል መግባታቸውን የሰማሁትም ባለፈው ሳምንት ነበር። ህክምና ላይ እያሉ ሚያዚያ 25፣ 2012 ዓ.ም በ77 ዓመታቸው አርፈዋል። ዶ/ር በላቸው ለህዝብና ለሙያው ባደረጉት አስተዋጽኦ ሲታወሱ ይኖራሉ።
ፈጣሪ ነፍስዎን በአፀደ ገነት ያሳርፍ‼️

ዘላለም ጥላሁን አ.ፕ አ.አ ዩኒቨርሲቲ