ወንጭፋችን ባዶ
ጎልያድ ከማዶ
ከእጆቼ አታመልጡም
እያለ ቢፎክር
ቢሸልል ቢያቅራራ
በድሮ ልማዱ
ከአሮጌ ሰማይ
ላይ ነጎድጓድ
ቢያጓራ
ደመና ፀንሶ
እሣት ወይ
ነበልባል በረዶም
ቢያፈራ
ጦርነቱ ከባድ
ቀበቶ ሚያስፈታ
የብዙ ጓዶችን
እስትንፈስ የገታ
ለመግለፅ የሚከብድ
ለወሬ አስቸጋሪ
በሩቁ ለሚያዩት
ቢሆንም አስፈሪ
እኛ ግን
ተርፈናል ይመስገን
ፈጣሪ
አልሃምዱሊላሂ
ከፍ ይበል
ንጉሡ
ምጡን እርሱትና
ልጃችሁን አንሡ
ተደሰች ተደሰት
ጨፍሩ ደንሡ
በአሸናፊነት
ድል ከፍ
ይበል ጽዋችሁ
አቮ
ደስ ብሎኛል
እንኳን ደስ
ያላችሁ
©ዶ/ር
ጌታነህ ካሴ
ኅዳር 3/2011 ዓ.ም
No comments:
Post a Comment