ከድንክ አልጋዬ ላይ
ህልም አይቸ ማታ
የባ'ል ገበያ ውስጥ
የትዳር ገበታ
መበልት ወይዛዝርት
ስሜት ተጋሪዎች
ፍቅርን በድቃቂ ሳንቲም
መንዛሪዎች
ምን አልባት ወደ ፊት
ሴተኛ አዳሪዎች
ይህ አይመጥንሽም ይህም
አይሆንሽም
ቅቅል አይጋብዝም ክለብ
አያመሽም
ያኛው ዝምተኛ ዝጋታም
ኮስታራ
ሁል ጊዜ ቁምነገር
ቀልድ የማያወራ
ቀብራራ ገጠሬ ቪላ
ቤት የሌለው
ገና በማህፀን አምላክ
የበደለው
እያሉ በህብረት በማበር
ሲዞሩ
በትዕቢት በጉራ እንደተወጠሩ
ከደራው ገበያ ጥሪት
ሳይሸምቱ
በጠራራው ፀሐይ እንዲያ
እንደዋተቱ
አንዳቸው ሳይዘግኑ
ብፌው ባዶ ሆነ
ሰዓቱ መረሸ ገቢያው
ተበተነ
ምሱ ፆም ማደር ነው
መውደድን በወረት በብር
ለተመነ
ማሳሰቢያ : ህልሜ ወደ ትንቢትነት
ከመቀየሩ በፊት ልብ ያለሽ ልብ በይ ።