መላዋ
እየሩሳሌም የጩኸት ድምጽ ይሰማባታል፤ከወትሮዋ
በተለየ ሁኔታ ጩኸት በዝቶባታል። ከወዲያ
ወዲህ እየተመላለሱ ህዝቡን የሚያሳምፁ ካህናቱና
ሊቃነ ካህናቱም ወገባቸውን ታጥቀው
ይመላለሱባታል። የከተማዋን ሽብር የተመለከቱ
ሁሉ የገበያ ቀን ነበርና ግራ ተጋቡ በሚሰሙት
ጩኸት ተደናገሩ፣የጩኸቱን ምክንያት ተረድቶ
ማስርዳት የሚችል ግን አንድም ሰው የለም ብቻ
ሁሉም ይጮሃል። በመንገድ
አልፈው የሚሄዱትም "ቤተመቅደስን አፍርሰህ
በሦስት ቀን የምተሰራው" እያሉ ይጮሁ
ነበር። ከቤተ መንግስትም ሆነ ከቤተ ክህነቱ
ባለስጥናት ጩኸቱን ለማስቆም የደፈረ
ማንም የለም። ሦስት ዓመት ከሦስት ወር በተደረገው
ተዓምራት በሕሙማን አድረው ይጮሁ የነበሩ
አጋንንት ዛሬ ደግሞ በአይሁድ ልቡና አድረው
ይጮሃሉ። ጩኸቱ ግን ይለያያል። ያን ጊዜ" ልታሳድደን መጣህን? "የሚል ሲሆን ዛሬ ግን "ስቀለው!
ስቀለው!" የሚል ሆኗል። ነገሩ እየጠነከረ መጥቶ የጩኸቱ ምክንያት የሆነው ንጉሠ አይሁድ
ኢየሱስ ክርስቶስ ታስሮ ወደ ሊቀ ካህናቱ ግቢ
ደርሰ።
ሊቀ ካህናቱ ሀና የሥልጣን ዘመኑን
ጨርሶ ለቀያፋ ያረከበ ቢሆንም ስለሽምግልናው
በጀመሪያ በተከሳሹ ላይ ፍርድ እንዲሰጥ
የተጠየቀው እርሱ ነበር። ነገር ግን እርሱም
ቢሆን ጩኸቱ ለማስቆም አቅም አልነበረውም። ሲጀመርም
ጩኸቱን መርቆ የከፈተው ማን ሆነና? የእርሱ
የልጅ ባል ቀያፋ አይደለምን? "ስለ ህዝቡ ሁሉ
አንድ ሰው ቢሞት ይሻላል" ብሎ። በዚህ በሊቃነ
ካህናቱ የተጀምረው ጩኸ ወደ ሕዝቡ ወረደ በሊቀ
ካህናቱ ግቢ የፍርድ ሂደቱ እየተካሄደ ባለበት
ወቅት ሌላ አዲስ ጩኸት ተከሰተ ፤የሰባኪው
ዶሮ ጩኸት ተከሶ የመጣው የክርስቶስ
ፍርድ ሳይጠናቀቅ ደቀመዝሙሩ ዼጥሮስም ተከሶ
ቆመ። በሕሊና ዳኝነት ወንጀለኛ መሆኑ ስለተረጋገጠ
ምስክር እንኳን ሳያስፈልገው እራሱ በሰጠው
የእምነት ቃል ማስረጃነት ዳኛው አስቸኳይ
ውሳኔ ስለሰጡ ዼጥሮስ ስለራሱ እያለቀሰ
ወጣ። ምንላባትም የጩኸቱ ምስጢር ገብቶት
ስለራሱ ይጮህ የነበረ ብቸኛ ሰው ሳይሆን
አይቀርም። ሌሊቱን በሙሉ አንድ ጊዜ እንኳን
ሳይተኙ በጩኸት ከሐና ወደ ቀያፋ ከቀያፋም
ወደ ሐና እያመላለሱት ሲጮሁ አደሩ። ሲነጋም
የካህናት አለቆች ከህዝቡ ሁሉ አሉ የትባሉትን
ሽማሌዎች ጠርተው የሞቱን ጦማር አጸደቁት
። ከሳሽ ሳይኖር በደሉ ሳይዘረዘር እንዲሞት
የተወሰነበት የመጀመሪያ ሰው።