ላንቺ ይባልኝ እንጅ ቃልሽ ለፈረሰው፣
እኔስ እኖራለሁ እንደ ሰው እንደ ሰው። አዎ! ላንቺ ነው፤ ከገባሽ ይግባሽ
አዎ! ላንቺ ነው፤ ሳምንሽ ለከዳሽኝ ድንገት የተግባባን መስሎኝ ልቤን ሰጥቸሽ ዘነጣጥለሽ ላስረከብሽኝ።ይሄው!
ይሄው! እድሜ ላንቺ የተሰበረ ልቤን ጥገና ያልሄድሁበት ያልዞርሁበት ቦታ የለም።ግን መድሃኒቱ ካንቺ ዘንዳ ሆኖ
ከየት አባቴ እንደማገኘው ግራው ገብቶኝ ስጨነቅ እኖር ነበር። አሁን ግን እግዚአብሔር ይመስገን ልቤ ወደ ነበረበት
ተመልሷል።እንዳንቺማ ቢሆን ኖሮ ልቤን አጥቸ እየተሰቃየሁ እኖር ነበር። ግን ፈጣሪ አለሁልህ አለኝ።ታስታውሻለሽ ያኔ በፊት በፊት የሰማዩን ከዋከብት የምሽቱን ጨረቃ የቤታችን አምፖል አንቺ ሆነሽ የምበላበት ሳህን
የምማርበት ደብተር ዉስጥ እየተገኘሽ ሰላሜን አሳጥተሽኝ በህልሜም እየመጣሽ እንቅልፍ ነስተሽኝ ነበር።ጨረቃም ከዋከብትም አምፖልም ሳህንም አንቺው ሆነሽብኝ
ይህችን አለም ላንቺ አድርጌ ስያት ነበር።ለካ አንቺ ለዚችች አለም ኢምንት! ኢምንት! ኢምንት! ነሽ።አሁን ላይ ግን
ልንገርሽ ውዴ!ጨረቃውም ጨረቃ ከዋከብቱ ከዋከብት አምፖሉም ሳህኑም ያው ራሳቸው ናቸው። ለካ ያኔ አእምሮየ ውስጥ አግዝፌ
ስየሽ ስለንነበር ነው እንደዚያ ራሴን ጥየ ስሰቃይ የኖርሁት።ግን እንዴት አስቻለሽ ያን ሁሉ ስቃየን ያን ሁሉ
ጭንቀቴን ያን ሁሉ ችግሬን እየነግርሁሽ፤ ትንሽ ሰወኛ ስሜት ያልተሰማሽ ለምን ነበር? ምላሹን አልፈልገውም። ጽፈሽ
ያዥው ይጠቅምሻል።የሆነው ሆኖ ለህይወቴ ትልቁን ትምህርት ሰጥተሽኛል።ተሰብራ የነበርችውን ልቤን ድጋሜ
እንዳትሰበርብኝ አርቄ እንዳስቀምጣት ስለረዳሽኝ አመሰግናለሁ።በተረፈ የእጅሽን ይስጥሽ አልልሽም።ምክንያቱም የዛሬን
አያርገውና በአንድ ወቅት ለህይወቴ መሰርታዊ ከሆኑት ነገሮች ማለትም ምግብ፣ መጠጥ፣ መጠልያ እና ልብስ ጋር
ተደምረሽ የነበርሽ፤ ነገር ግን በራስሽ ምክንያት ራስሽን የቀነስሽ ሴት ነሽ።ስለዚህ ከልቤ ከልቤ የምመኝልሽ መልካሙን
ሁሉ እንዲገጥምሽ ነው።በተረፈ ይሄን ዘፈን ላንቺ ሳይሆን ለምስኪን አፍቃሪዎች ጋበዝሁኝ።
አፍቅሬ እያመንኩኝ ሳልጠላሽ፣
አስችሎሽ እምነቴን ከበላሽ።
ላንቺ መባል ይብቃኝ ከእንግዲማ፣
ሃገር ይወቅልኝ ሁሉም ይስማ።
ለፍቅርሽ ስጨነቅ ስጠበብ ከርሜ፣
ለክብርሽ ስሟገት ስምሽን አንግቤ፣
በዚያ በክፉ ቀን ሳጣሽ ካጠገቤ፣
ፍም ይወጣኝ ነበር እንደመንገብገቤ።
ያንችው አፍቃሪ
አምኖ የተከዳ መሪሪ ነው ሐዘኑ፡፡ ግን መድሐኒት ሲገኝ መልካም ነው፡፡ ያለፈው ህይወት ትምህርት ይሆናል ለሚመጣው ደግሞ እንዳይጎዳ እራሱን ያዘጋጃል፡፡
ReplyDelete