Friday, January 11, 2019
Monday, November 19, 2018
ስሜት ተጋሪዎች
ከድንክ አልጋዬ ላይ
ህልም አይቸ ማታ
የባ'ል ገበያ ውስጥ
የትዳር ገበታ
መበልት ወይዛዝርት
ስሜት ተጋሪዎች
ፍቅርን በድቃቂ ሳንቲም
መንዛሪዎች
ምን አልባት ወደ ፊት
ሴተኛ አዳሪዎች
ይህ አይመጥንሽም ይህም
አይሆንሽም
ቅቅል አይጋብዝም ክለብ
አያመሽም
ያኛው ዝምተኛ ዝጋታም
ኮስታራ
ሁል ጊዜ ቁምነገር
ቀልድ የማያወራ
ቀብራራ ገጠሬ ቪላ
ቤት የሌለው
ገና በማህፀን አምላክ
የበደለው
እያሉ በህብረት በማበር
ሲዞሩ
በትዕቢት በጉራ እንደተወጠሩ
ከደራው ገበያ ጥሪት
ሳይሸምቱ
በጠራራው ፀሐይ እንዲያ
እንደዋተቱ
አንዳቸው ሳይዘግኑ
ብፌው ባዶ ሆነ
ሰዓቱ መረሸ ገቢያው
ተበተነ
ምሱ ፆም ማደር ነው
መውደድን በወረት በብር
ለተመነ
ማሳሰቢያ : ህልሜ ወደ ትንቢትነት
ከመቀየሩ በፊት ልብ ያለሽ ልብ በይ ።
Saturday, November 17, 2018
.....ላንቺ....
የብዕሬ
ጠብታ ላንቺ
የሚመጥን ባይሆንም
ቀለሙ
በሄድሽበት ሁሉ
እንድታስታውሽኝ እስከ
ዘላለሙ
ፃፍልኝ ያልሽኝን
ያው ተቀኘለሁልሽ
በግሩም ተፈጥሮሽ
ስፍስፍ ብልልሽ
መናኝ በሚያስቱ
አስማታም
ጥርሶችሽ
ቀልብን በሚያሣጡ
ምትሃተኛ ዓይኖች
አንኳን ሁለት
ስንኝ እንኳን
ስምንት ቀለም
ህይወት ብታስከፍይ
ላንቺ ብዙ
አይደለም
አይመረመሬው የሠራሽ
ተጠቦ
የውበት ተምሣሌት
ጠይም የደም
ገንቦ
የሥብዕና ጥግ
የሴትነት ልኩ
ምን ብዬ
ልግለፅሽ እንዴው
በምን መልኩ?
ታዲያ ለዚህ
ገላሽ ለዚህ
ውብ ተፈጥሮ
ስምሽ ግንባሬ
ላይ በደማቅ
ተወቅሮ
አገልጋይሽ ልሆን
አምላክ ቢፈቅድ
ኖሮ
ደከመኝ ሰለቸኝ
አልልም
ነበረ
ዳሩ ምን
ዋጋ አለው
ምኞት ሆኖ
ቀረ
©ዶ/ር
ጌታነህ ካሴ
ኅዳር 7/2011 ዓ. ም
እንኳን ደስ ያላችሁ
ወንጭፋችን ባዶ
ጎልያድ ከማዶ
ከእጆቼ አታመልጡም
እያለ ቢፎክር
ቢሸልል ቢያቅራራ
በድሮ ልማዱ
ከአሮጌ ሰማይ
ላይ ነጎድጓድ
ቢያጓራ
ደመና ፀንሶ
እሣት ወይ
ነበልባል በረዶም
ቢያፈራ
ጦርነቱ ከባድ
ቀበቶ ሚያስፈታ
የብዙ ጓዶችን
እስትንፈስ የገታ
ለመግለፅ የሚከብድ
ለወሬ አስቸጋሪ
በሩቁ ለሚያዩት
ቢሆንም አስፈሪ
እኛ ግን
ተርፈናል ይመስገን
ፈጣሪ
አልሃምዱሊላሂ
ከፍ ይበል
ንጉሡ
ምጡን እርሱትና
ልጃችሁን አንሡ
ተደሰች ተደሰት
ጨፍሩ ደንሡ
በአሸናፊነት
ድል ከፍ
ይበል ጽዋችሁ
አቮ
ደስ ብሎኛል
እንኳን ደስ
ያላችሁ
©ዶ/ር
ጌታነህ ካሴ
ኅዳር 3/2011 ዓ.ም
Friday, September 28, 2018
ውረድ ከመንበሬ
ምነው ይጨንቀኛል ባርባር
ይለው ሆዴ?
ትውልዴ ተቆጥሮ ልሳኔ ተጣርቶ ላይቀር መታረዴ
ምነዋ መስገብገብ ለነፍሴ
መጓጓት መኖርን መውደዴ?
ወልዳ መሳም ላትችል
ነፍሰ ጡሯ እናቴ
እስከ መቼ ድረስ
አንገቴን ላቀርቅር
ይንበርከክ ጉልበቴ
ሰላም ላውርድ ብዬ
ሀገር ላቅና ብዬ
ፈገግ ብዬ ባቅፍህ
ደስ ያለኝ መስዬ
ያረድኸው ወንድሜ ደሙ
ሲከረፋኝ
መግደል መሸነፍ ነው
ብለህ ብትደልለኝ
እንዴት አልናደድ እንዴትስ
አይከፋኝ
እንዴት አይዘን ልቤ
እንዴት አይገምልለኝ
በርግጥ አውቂያለሁ
ገብቶኛል ጥፋቴ
ሀገሬን ለቁራ አደራ
መስጠቴ
የቁራ ልጅ ቁራ ቁራ
የወለደው
ከመገንባት በፊት ማፍረስ
የለመደው
አመራር ላስተምር አገዛዝ
ላለምደው
ሀገር አቅና ብዬ መንበር
ላይ ብጥደው
መሰረቱን ጣለ
ቤት ሊሰራ ነው ስል
ያው መልሶ ናደው
የባለጌ ክንዱ ቢሆንም
ደንዳና
ማፈራረስ እንጅ መስራት
የት ያውቅና
የጋለሞታ ልጅ ያልተቆነጠጠ
ተለቅቆ ያደገ ተሳድቦ
እየሮጠ
አጥፍቶ በመጥፋት ሆኖ
አስተዳደጉ
መናድ ይመስለዋል የነጻነት ጥጉ
ውረድ ከጫንቃዬ ከእንግዲህ ይበቃል
የሚያጠግብ እንጀራ
ሊጡ ያስታውቃል
እርካቤን ወዲህ በል
ውረድ ከመንበሬ
አርማዋ ከፍ ይበል
በደም ያቆየኋት ኢትዮጵያ ሀገሬ
ኪቶ:መስከረም 8/2011 ዓ.ም
Monday, August 20, 2018
እንትን አፍጥ

አሁን የቆምሁባት ተራራ እንትን አፍጥ ትባለለች። “ተራራ ሲወጡ የሚፈጥባቸው ነገር አለ እንዴ?” የሚለውን ጥያቄ ለሴቶቻችን እንተወውና እዚች ተራራ ላይ ቆሜ አንድ ጊዜ ወደ ላይ አንድ ጊዜ ወደ ታች እያፈጠጥሁ ነው። የሚታየው ሁሉ እጅግ ይማርካል ሊያዘረዝር የተዘጋጀ የገብስ ቡቃያ፣ የተዳገረ ቦቆሎ፣ የለሰለሰ የጤፍ መሬት እርሻ ። ኧረ በወላዲተ-አምላክ እዚጋ ደግሞ በግራ ጎኗ እቅፍ ሙሉ እንጨት የያዘች ልጃገረድ፣ በአርባ ሽንሽን ቀሚስ ውስጥ ከፍ ዝቅ የሚል ትልቅዬ መቀመጫ፣ያለ ጡት ማስያዣ የቆመ አጎጥጎጤ ጡት፣ ሊፕስቲክ አይቶ የማያውቅ ሳሙኝ ሳሙኝ የሚል ከንፈር፣ ፣ የሚሽኮረመሙ ዓይኖች ፣ ባለ ዲምፕል ጉንጭና ባለ ንቅሳት ግንባር ወይኔ ቀጭኑ ማበዴ ነው መሰል!
በመሄድና በመቆም መሀል ፈዝዠ ይኸን ሁሉ ስመለከት የመነኩሴ ምራቅ የሚያህል የዝናብ ጠብታ መሀል ጆሮዬ ላይ ሲላተም የፈጠረው አሰቃቂ ድምጽ ከቁም ቅዠቴ ቀሰቀሰኝ። ድምፁ ሁሉንም የታች ቤት ነዋሪዎች ያስደነገጠ ነበር። አንዳንድ ቧልተኞች እንደሚሉት ከሆነ አማኔ ሊጠጣ ወደ አፉ ያለውን ቡና መልሶ “እሰይ አትሂድ ስለው ሲንቀለቀል ሂዶ አስገቡለት” ሲል ሰምቶ አንቱካ ምናባህ በማለት ተቆጥቶታል። መሲና ቅድስቴ ጸሎት ቤት ውስጥ የድንግል ማርያምን ሥዕለ አድህኖ ታቅፈው ተገኝተዋል። እንዳሌና ሲስተር አዘነጋሽ በአርምሟቸው ፀንተው ያሳለፉት ሲሆን ረቂቅ “ውይ ጌችዬን ምን ነክቶብኝ ይሆን” የሚል ቃል አምልጧታል። ስሌሎች የተጣራ መረጃ አላገኝሁም። እኔስ ምን ሆንሁ? እኔማ ወንድነቴን ልጅቱ እንድታይልኝ ፈልጌ ይሁን የአዲስ አበባው ጉዴ ትዝ ብሎኝ “ዘራፍ የበላይ አሽከር” ብዬ አካባቢውን ስቃኝ ማንም አልነበረም።
ባለፈው ቅዳሜ ዕለት አ.አ ከአውቶብስ ተራ ወደ ጎጃም በረንዳ በሚወስደው መንገድ እየተጓዝሁ አንዱ ሰላቶ በቀኝ ጎኔ በኩል (ያባቴ አምላክ ጎኑን ይንቀለውና) በጫማ ጥፊ መታ መታ ሲያደርገኝ ፊቴን እንደ መከራ አጥቁሬ ከፈረስ ጭራ በቀጠነ ድምጽ ስልኬስ አልሁት በግራ ጎኔ የቆመውን ግሪሳ። የፊቴ መኮሳተር አስፈርቶት ይሁን የድምፄ መቅጠን አሳዝኖት አላውቅም እሽ ብሎ ስልኬን መለሰልኝ። እኔም መንገድ ዳር ወድቆ ከማደር የጠበቀኝን አምላክ እያመሰገንሁ ወደ አዲሱ ገበያ በታክሲ። ከቅዳሜው ትዝታየ ስመለስ ልጃገረዲቱም ከአካባቢው ተሰውራለች። ዝናቡም መጣሁ መጣሁ ይላል፤ ጉርጥ ጉርጥ የሚያህል የዋልካ ጭቃ እየዘለለ ቦት ጫማየ ውስጥ ይከተታል፤ እኔም ጉዞዬን ቀጥያለሁ።“ጉች ጉች ያለ ጡት በል ደህና ሰንብት አንተን ማግኘት ርቋል ከዕለተ ምፅዓት” የሚለውን ዘፈን እያንጎራጎርሁ።
ሾላሜዳ:ሐምሌ 13/2010ዓ.ም
Subscribe to:
Posts (Atom)


