Thursday, October 19, 2017

ዝጎራ

ረዥም የአማርኛ ጽሑፍ ስታዩ የሚያስነጥሳችሁ ወይም ነስር የሚያስቸግራችሁ ወገኖች ይህንን ጽሑፍ ያለማንበብ ብቻ  ሳይሆን ያለማየት መብታችሁ የተጠበቀ ነው። በእኔ የህይወት ሚዛን ላይ ግን “after many years of struggle now I am your qualified doctor” ብሎ በፖሰቱበት ምሽት ባላገሩ ቢራ ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ በደሌ ከዋሊያ እየቀላቀሉ ሲገለብጡ አምሽቶ፤ እንደ እንክርዳድ ጠላ አፍገምግመው በሚጥሉ ጥያቄዎቻቸው አለማወቃችንን አውቀን እንድናልፍ ያደረጉንን ግለሰቦች ሳይቀር “እከሌ ጮማ፣ እናትህን እንዲህ ላርጋት” እያሉ አስነዋሪ የስድብ ናዳ እያወረዱ ከመግባት ይልቅ ይኸኛው የተሻለ አማራጭ ይመስለኛል።

ከባለ ምጡቅ  አእምሮው ገፀ ባህርይ ጋር ምስጢረኞችን እጽዋት ፍለጋ በሊማሊሞ ገደል  መነሳት መውደቁ፤ እንደ እሳት በሚያቃጥል የጋለ መሬት ላይ በባዶ እግር መጓዙ ። ከእኒያ በፍጹም ስውራኑ እና በክሱታኑ መካከል ያሉ ትልቅ አባት የሚወጡ ነፍስን የሚያለመልሙ ምክሮችን መስማቱ። "ኢትክስት ወኢትንግር ስመ ዝ ጎራ እስመ አኮ መካነ ሁከት ወነጎርጓር ዘእንበለ መካነ ጸሎት ወአርምሞ" የሚለውን ደብዳቤ በፍጹም ተመስጦ ማንበቡ

ፍላጎቱ ያላችሁ ብቻ ታነቡት ዘንድ የምጋብዛችሁ ታሪክ የተፈጸመው ከደብረ ታቦር ከተማ 78ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኝ አንድ ትልቅ ተራራ የበቀለ ደን ውስጥ በሚገኘው ቤተክርስቲያን ነው ።

...ይህን እየተነጋገርን እያለን ግርማ ሞገሳቸው 
የሚያስፈራ 
ረዘም ያሉ አዛውንት መነኩሴ ከወደደኑ አካባቢ ብቅ ሲሉ ሁሉም በአክብሮት ራስቸውን ዝቅ እያደረጉ በመስቀላቸው ተሳለሙ ።የሆነ ብርሃን የከበባቸው ይመስላሉ።አንዳች ነገር ገፋፋኝና ከእግራቸው ስር ወድቅሁ። ትክሻየን ይዘው ቀና አደረጉኝና በመስቀላቸው አሳልመው ግንባሬን ሳም አደረጉኝ ።መላ ሰውነታቸው ዕጣን ዕጣን ይሸታል።

ቢጫ የመናኝ ልብስ ቀኝ እጃቸውን አውጥተው አጣፍተዋል።ከወገባቸው በላይ ትክሻቸው ላይ በከፊል ልብስ አልለበሱም።የፊታቸውና የትክሻቸው ቆዳ ቀለም የቀይ ዳማ የሚባል ሲሆን የፊታቸው ቆዳ ዓይናቸው አካባቢ ከመሸብሸቡ በስተቀር በምቾት የሚኖቱ እንጂ በምናኔ ያሉ አይመስልም።የምንኩስና ቆባቸው በሰሌን ተስርቶ በቆዳ የተለበደ ነው።ከምንኩስና ቆባቸው አምልጦ የወጣው ጥጥ መሳዩ ፀጉራቸው  ከትክሻቸው ላይ እንደሐረግ ተጠማዞ ተኝቷል።የፊታቸው ፂም እንዲሁ ረጅም ሪዝ ሆኖ አንገታቸውን ሸፍኖታል።ደረታቸው ላይ የመባረኪያ መቀል ያንጠለጠሉ ሲሆን ቀኝ እጃቸው ላይ እስከ ክንዳቸው ድረስ ከዕንጨት የተሰራ መቁጠሪያ ተጠምጥሞበታል።በእጃቸው ለአባ መዝገበስላሴ የሰጠሁዋቸውን የዕፆች ቅርንጫፎች ይዘዋቸዋል።የገረመኝ ነገር ግን እኔ ስሰጣቸው እንደጠወልጉት ሳይሆን ፍጹም ለምልመው ነበር።

የፊታቸው ጸዳል የሚለግሱት የትሕትና  ፈገግታ አንዳች መግነጢሳዊ  ሀይል ያለው ቢሆንም ግርማቸው ደግሞ የሸብራል።አባ መዓዛ ቅዱሳን ወደ ጆሮየ ጠጋ ብሎ በለሆሳስ "በፍጹም ስውራኖቹ እና በእኛ መካከል ያሉ አባት ናቸው።በዚህ ወቅት ልታገኝ የምትችለው እኒህን ታላቅ አባት ነው ።የምትፈልገውን መጠየቅ ትችላለህ" አለኝ። ፈዝዤ እንደቆምሁ ፈገግ አሉና "የኔ ልጅ ቃላችንን አክብረህ ትእዛዝችንን በድካምህ ስለፈጸምህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁንልህ" አሉና "የሆነው ሆነና ያን ሁሉ ድካም ደክመህ ትእዛዛችን የፈጸምከው ምስጢራችንን ለማወቅ ባለህ ጉጉት ነው ወይስ የዕድሜህ ማጠር አሳስ ቶህ ነው? አሉኝ ።

አባታችን ሞትን የፈራሁት መሰለኝ አልኋቸው "እውነት አለህ የእኔ ልጅ ይሁንና ሞትን ብትፈራውም ብትንቀውም የማይቀር ዕዳ ነው ።የዕድሜህ ማጠር ወይም መርዘም አያስጨንቅህ የፈጣሪ ፈቃድ ነውና ።ይልቁንም በተሰጠችህ እያንዳንዷ ቀን በመልካምና በድስታ ለመኖር ስጋህን ተጠንቀቀው ፣ነፍስህን ቁጠራት፣እምነትህ ን ትሀንቅቀው" አሉና ቀጠሉ።እኔ ብቻ ሳልሆን ሁሉም በተመስጦ እያዳማጡ ነበር። "ኢትዮጵያዊነት በ አምስት አምዶች የታነጸ መኖሪያ እልፍኝ ነው ።ጥልቅና ሰፊ እውቀት ፣መዛል የሌለበት ትጋት፣በትዕግስት የታሸ ጀግንነት ፣ርኩሰት የሌለበት ቅድስና፣ግብዝነት የሌለበት ምስጢራዊ ህይወት ነው።"

"የምስጢር ሙዳይ ሁን እንጅ የእሳት ማንደጃ ወናፍ አትሁን ።ሰዎች ሊሰሙህ በሚችሉት ችሎታቸውና ፍላጎታቸው መጠን ብቻ ተናገር ፣ቁጥብ እንጂ ዝርው አትሁን ።ለእውቀት ትጋ።በከፊል በተረዳሃው ነገር ራስህን እንደ አዋቂ አትቁጠር ።በከፊል ከማወቅ አለማወቅ ይሻላል።ስራ ስትሰራ ደግሞ ነገ ትቼው ለምሞተው ወይም ብሰራ የሚጠቀመው ሌላ ነው በሚል ተስፋ ቢስ ሆነህ ሳይሆን ዘላለም እንደምትኖር
ክል በመትጋት ነው ።ትጋት ጥሩ ነው ።ችኮላህ ግን ውጤት አያመጣም፣በችኮላ መስራትና በፍጥነት መስራት የተለያዩ ናቸው ።ርኩሰት የዕውቀትና የስልጣኔ መገለጫ አይደለምና ማንነትንና ሰብዓዊ ክብርን ከሚያጎድፉ ተግባራት መታቀብን ገንዘብ አድርግ።

እናም በእየ ዕለቱ በኑሮህ ጠንቃቃ ሁን ።ያለጸጸት ነገን ለመኖር ዛሬን በቁም ነገር አሳልፍ።ውሳኔዎጭችህን መርምር፣ልክ እንደገና ህይወትን የመኖር ዕድል ቢኖርህ ደግመህ የምትኖረውንና ለማከናወን የምትመርጠውን ዐይነት ህይወት ለመኖር ሞክር ።እንዲህ ያለ ጥያቀ ብትጠየቅ ምልስህ ምንድን ይሆን? እንደገና የመወለድ ምርጫ ቢኖርህ ኢትዮጵያ ውስጥ ኢትዮጵያዊ ሆነህ ለመውለድ ትመርጣለውህ? የያዝከውንስ ሙያ በድጋሜ ትመርጠዋለህን? ያገባሃትን ሚስትስ እንደገና ታገባታለህ? ወይስ መነኩሴ ከሆንህ እንደገና የምንኩስና ህይወትን ትደግመዋለህን?" አሉና እፆቹን ወደ አፍንጫቸው አስጠግተው እንደ ማሽተት አደርጉ።

"ዕፁን ለምን እንድታመጣ እንደፈለግን ብርቱ ምስጢር ነውና  ወንድምህ አባ መዓዛ ቅዱሳን ወደፊት ይነግርሃልና በልብህ ጠብቀው።በእምነትህና በትጋትህ ልክ የስራ ድርሻ ይኖርሃል።ፈ
ሪ ምህረቱንና ጸጋውን ያብዛልህ ።ወላዲተ አምላክ አትለይህ።"ብለው ትክሻየ ላይ በግራ ዕጃቸው  ማጣፊያ ስር ይዘውት የነበረውን ምርኩዛቸውን በቀስታ ል ሲያደርጉብኝ በቀስታ ልቤን ጉትት አድርጎ ሲወስደኛና ራሴን ለመሳት ሲከጅለኝ ታወቅኝ።ዐይኖቼ የቀስተደመና ቀለማትን ከደኑ ላይ  የሚያዩ መስለኝ።ምን ያክል ሰዓት እንደቆየሁ አላውቅም ደስ የሚል የሰላም እንቅልፍ ወስዶት እንደቆየ ሰው ከድካምና ከቁስል ጥዝጣዜ ስሜት ነፃ ሆኜ ተነሳሁ።



ምንጭ፦ዝጎራ በአለማየሁ ዋሴ እሸቴ


Sunday, October 15, 2017

ታላቅ የምስራች

ታላቅ  የምስራች ለደስታዬ ተካፋዮች በሙሉ እነሆ ያኔ ገና  በልጅነት እድሜ በግ እና ፍየሎችን እየጠበቅሁ ያኸለምሁት ህልሜ  እውን መሆኑን  ምክንያት በማድረግ ከዛሬ ጀምሮ ብሸከም የማልችለውን  ማዕረግ ከፊት በማስቀደም ዶ/ር  ጌታነህ ካሴ ተብዬ እንድጠራ የተፈቀደልኝ መሆኑን ስገልጽላችሁ በታላቅ ደስታ  ነው። ዘወትር  ከጎኔ ሁናችሁ አይዞህ እያላችሁ ለዚህ ታላቅ ክብር እንድበቃ ላደረጋችሁኝ ወንድሞቼና እህቶቼ በሙሉ ውለታችሁን ከፍየ አልጨርሰውምና  እግዚአብሔር ዋጋችሁን  እጥፍ ድርብ አድርጎ ይክፈላችሁ  እላለሁ። እውነት ለመናገር በዚህ ሰው አምላኩን ረስቶ  ገንዘቡን ማምለክ በጀመረበት ዘመን “መወለድ ቋንቋ ነው” የሚለውን ብሂል በተግባር ያሳያችሁኝ ለእኔ የተሰራችሁ የፍቅር ጣኦታት  ናችሁና ሳመሰግናችሁ ውየ ሳመሰግናችሁ ባድር አይወጣልኝም። ተምሮ ሰው ይሆንልኛል በሚል ተስፋ ከእለት ጉርሳችሁ ይልቅ ለእኔ በማድላት ላስተማራችሁኝና ጠንቅራችሁ ብርታት ለሆናችሁኝ ቤተሰቦቼ ደስ ብሎኛልና ደስ ይበላችሁ እላለሁ። በቸርነቱ ብዛት ለዚህ ያበቃኝ አምላክ ከእናቱና ከቅዱሳኑ  ሁሉ ጋር ክብርና ምስጋና ይድረሰው። አቤቱ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ  የልመናየን ቃል ሰምተኸኛል እና  አመሰግንሃለሁ። ድንግል ሆይ አንቺ የጽርሐዓርያም ብርሃን ከጎኔ ሆነሽ ታረጋጊኝና ግርማ ሞገሥ ትሆኝኝ ዘንድ እኔ ማን ነኝ
      መች ተነግሮ ያልቃል ያምላክ ቸርነቱ
እኛስ ብለን ነበር ቀረን ሆነን ከንቱ
በፍፁም ትሕትና አሃዱ ቢል ቄሱ
በመልካም ውብ ዜማ ስሉስ ቢቀደሱ
መንቨሩ ፊት  ብትቆም ደጓ የዓለም ቤዛ
አምላክም በፋንታው ምህረቱን  አበዛ
በሃያል ስልጣኑ ጥልን  ደመሰሰ
ያጣነው ልጅነት ዳግም ተመለሰ
መለያየት  ቀረ ውላችን ታደሰ
እረኞች ዘመሩ ፍጥረት ተደመመ
በህይወት  አዳራሽ  ማህሌት ተቆመ
Dr. Getaneh Kassie