Friday, March 31, 2017

amira's letter 1

I recieved the following emails some three weeks back from one of my friends on facebook . Now I am going to post it subsequently so that you guys in the social media specially Ethiopians and newcomers are aware of the presence of such kind of game and take care of your money and time.the game begins like this "How are you today Dear? I am very happy to be your true friend. please write me on my email(amiraibran@gmail.com) so that I can tell you many things about me and attach my photos Yours amira ibrahim" and my response was "How are you Miss Amira I am very Happy to meet you too. here are my personal details and I am waiting for  your messages"
Yours Getane kassie

amira's letter 1

DARLING PLEASE I NEED YOUR ASSISTANCE
Dearest One,
Thanks for your Immediate response, How are you doing today? I hope all is fine and you're perfectly doing well in health. My name is Amira Ibrahim Fred.I am from Libya Tripoli in North African. 24years old, 5ft 8inches tall,Single never married, black hair and brown eyes. I want to assure you that Color, Race, Religion or Nationality makes no difference to me . What i see in people are their Personality and Character. I promise you all that makes up a defined and a refined LOVE and i have a special reason why i decided to contact you immediately after going through your profile which i was well satisfied with. I decided to contact you because of my urgency situation here. I am presently living in Senegal due to the Civil War fought in my country. My Father ( Dr Ibrahim Fred was the CHAIRMAN MANAGING DIRECTOR OF Fred & SONS INDUSTRIAL COMPANY IN THE CAPITAL CITY OF MY COUNTRY ( Tripoli ), Also the PERSONAL ADVISER to the former HEAD OF STATE, before the rebels attacked our house one early morning & kill him with my mother, together with My younger sister.

Wednesday, March 29, 2017

“ነው ብሎ ቢነግህ እህ.....? ጨምርበት”

“ነው ብሎ  ቢነግህ እህ.....? ጨምርበት” ይላል የሀገሬ ሰው ከደቂቃዎችበፊት አንድ ጓደኛዬ facebook ላይ አገኘኝና የሚከተለውን መልእክት ላከልኝ ።
“የእመቤታችን የቅድስት ድንንግል ማሪያም መልዕክት::በአውሮፖውያን አቆጣጠር በ 1994 ዓ.ም 2ኛ ወር ላይ በክፍለ ሀገር በየጉላቪያ ጠንክራ የሆናችሁ ልጆች ዛሬ ላመሰግናችሁ ለጸሎታችሁ ስለገባችሁት ጦርነት ተጀምሮ እስኪጨርስ ካጠገባችሁ ነኝ ፡፡ ለሁላችሁም ለእያንዳንዳችሁ እባካችሁ በርትታችሁ ከ እግዛብሄር እናንተም ፀልዩ /3 ጊዜ/ በቅዱስ ዮኀንስ ማርቆስ ሎቃስ ማቴዎስ
አባታችን ሆይ በሰማያት የምትኖር ስምህ ይቀደስ መንግስትህ ትምጣ ፍቃድህ በሰማያት እንደሆናቺ እንዲሁም በምድር ላይ ትሁን የእለት እንጀራችንን ስጠን ዛሬ በደላችችንን ይቅር በለን እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል አቤቱ ወደ ፈተናም አታግባን ከክፍ ሁሉ አድነን እንጂ መንግስተ ያንተ ናትና ኀይል ክብር ምስጋና ለዘላለሙ አሜን፡፡

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ሆይ በ መላኩ በ ቅዱስ ገብርቄል ስላምታ ስላም እልሻለሁ በሀሳብሽ ድንግል ነሽ በስጋሽም ድንግል ነሽ የ አሽናፌ የ እግዛብሄር እናት ሆይ ስላምታ ላንቺ ይገባሻል ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ አንቺ የተባርክሽ ነሽ ጸጋን የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ልዑል እግዛብሄር ከአንቺ ጋር ነውና ከተወደደው ልጂሽ ከጌታቺን ከመድኃኒታቺን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታና ምህርትን ለምኝልን ኃጤታችንን ያስተርሰርይልን ዘንድ ለዘላለሙ አሜን / 3 ጊዜ/

ይሄ የሆነበት ቦታ በዞና ሰሜን ኢጣልይ ነው። ይሄንን መልዕክት 24 ጊዜ አባዝቶ ለወገንህ አድርሱ።ከጨርስክ ከ 18 ቀን በኃላ ውጤቱን ውሽት አይምሰላችሁ።

1ኛ ክርሰትና ትባላለች ይህ መልዕክት ደርሷት አነበበችና እንደ መልዕክቱ መሰርት 24 ኮፒ አድርጋ በተነችው ከጨርሰች በኃላ ሚሊዮን ዶላር አገኘች፡፡

2ኛ ኦፒረሪሳት የተባለው እሱም ይህ መልዕክት እንደደርስው ተቀብሎ ቀዶ ጣለው ከዚያን ግዜ ጀምሮ ህይወቱ ተበላሽቶ ኑሮው ተመሰቃቅለ እና ካናዳ ሄዶ ሞተ፡፡

3ኛ ፋራንክ የተባለ ግለሰብ ይህ መልዕክት እንደደርስው 24 ጊዜ እንድታባዛለት ለ ሴክትሪዋ ሰጣት እሷም ለራሷ ወሰዳ 24 ጊዜ አባዝታ ጨርሰች ከዚያ በኃላ የተመሰቃቀለ ኑሮዋም ተስተካከለ፡፡

4ኛ አንዲት የቢሮ ሰራተኛ ይህ መልዕክት ደርሷት ተቀብላ ከርሳች ከ 18 ቀን በኃላ ከስርዋ ተባርርቺ በኃላም አስታወሰቺና ወርቀቱን 24 ጊዜ አባዝታ ካሰራጨቺ በኃላ የተመሰቃቀለ ኑሮዋ ተስተካክሎ ሚሊየነር ሆነቺ፡፡

5ኛ በአዲስ አበባ አካባቢ በቡራዪ ከተማ አንድ ግለሰብ ይህ መልዕክት እንደደርስው 24 ጊዜ አባዝቱ ካሰራጨ በኃላ መኖሪያ ቤት ስርቶ የተመሰቃቀለ ኑሮው ተስተካክሎለታል፡፡ይህ መልዕክት ተተርጉሞ ለመላው አለም መድርስ አለበት፡፡”

በቃ እንደ ዚህ የሚልነው።እና ለምን እንደላከልኝ ስጠይቀው እርሱም ሰው ልኮልኝ ነው አለ። ወዳጆቼ እኔ ግን እላችኋለሁ ማንም የፈለገውን ነገር የሚሞላበት ባዶ ማድጋ አትሁኑ።ለዚህ አይደል እንዴ “ነው” ብሎ ቢነግርህ እህ....? ጨምርበት የተባለው? እውነት ለመናገር እኛስ በfacebook ስሜን አላራባህም ብሎ ህይዎትን የሚያመሰቃቅል ጨካኝ አሊያም ደግሞ ለስሙ like & share ስለዘነበለት  ቢሊዬነር የሚያደርግ ወረተኛ አምላክ አይተንም ሰምተንም አናውቅ። ተወዳጆች ሆይ ይህን ማለቴ ግን የጸሎትን አስፈላጊነት ዘንግቸው እንዳይመስላችሁ።

Saturday, March 25, 2017

ወርቃማ አባባሎች

👉 የምንፈፅመው ጥሩም ሆነ መጥፎ ነገር የህልውናችን ነፀብራቅ ነው፤ስለሆነም እኛነታችንን ደብቀን መሰቃየት የለብንም፤መጥፎ የምንለውን አምቀን ጥሩ የምንለውን ብቻ የምንተነፍስ ከሆነ ውስጣችን ገምቶ ደማችን ይደፈርሳል።
👉 ለውጥ ማለት በጠባይም ሆነ በአሰራር ራስን መቀየር ፣አዲስ ሁኔታ ማምጣት ማለት ነው።ለውጥ በጽኑ ውሳኔ  ላይ የሚመሰረት  ራስን ለመቀየር  የመፈለግና የመነሳሳት ጠንካራ አቋምና ድርጊት ነው።ለውጥ ምኞትና ተስፋን የሚያዘወትሩ የማያዩት በራሳቸው መቆም የማይችሉና ድጋፍ ፈላጊ ደካሞች ደግሞ ምን ጊዜም የማይደርሱበት የውጤት መንገድ ነው።
👉 ከሰዎች ጋር በመኖር  የሰዎችን ችግር ለመፍታት መሞከርና መርዳት የተሻለ ጽድቅና  መንፈሳዊነት ነው። 
👉 ስህተትና በደል ከሰው ልጅ ጋር የሚኖሩ ደካማ ባህርያቱ ናቸው ። ስህተትን አውቆ መጸጸትና ከስህተቱ ለመማር መዘጋጀት ግን እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል፤በሕሊና ወቀሳ የቆሰለ ልቦናንም ያድናል ። 
👉 የአወዳደቁ አይነት በመለያየቱ እንጅ በእያንዳንዱ ሰው ውስጥ ውድቀት አለ፤ትልቁ ተግባር ግን ከወደቁበት መነሳትና  ራስን ማስተካከል ነው።
👉 ብቸኝነትህን የሚያመጣው ብቻህን መሆንህ አይደለም፡፡ አብሮህ ያለውን አለማወቅህ እንጂ፡፡ አካባቢህን ካላወቅህ በሰዎች መካከል ሆነህ እንኳን ብቻህን ትሆናለህ፡፡ አካባቢህን ካወቅከው ግን መቼም ብቻህን አትሆንም፡፡
👉 ራሷን ዝቅ ያደረገች ማሽላ  አንድም ከወፍ አንድም ከወንጭፍ ታመልጣለች።
👉 ለአንድ ሰው የስራውን ግብ ከፍ ፡ጊዜውን ደግሞ አጠር አድርገህ ከሰጠኸው የፈለግኸውን አከናውኖ ይቆይሃል።
👉 የሕጻንነት ወዳጇን የምትተው የአምላኳንም ቃልኪዳን የምትረሳ ሴት ቤቷ ወደ ሞት አካሄዷም ወደ ሙታን ጥላ ያዘነበለ ነው።ወደ እርሷ የሚገቡ ሁሉ አይመለሱም፥የህይዎትንም ጎዳና አያገኙም።
👉 ፍቅር በተዘጋ ቤት ውስጥ እንደሚያነዱት ሻማ ነው።በርና መስኮት ሲከፈት ሻማው ለንፋስ እንደሚጋለጥ ሁሉ ዓይንና ጆሮ ሲከፈት ደግሞ ፍቅር ለወሬኞች ይጋለጣል። 
👉 የፖለቲካ ጭቆና በበዛበት ሀገር ውስጥ፣ወሲባዊ ልቅነት የመጨረሻው የነጻነት አማራጭ ተደርጎ ይወሰዳል።አመንዝራነት ዜጎች ሌላው ቢቀር  ብልታቸው በመንግሥት ቁጥጥር ሥር አለመሆኑን የሚያሳዩበት መንገድ ነው።

Tuesday, March 14, 2017

አለቀች!

ያኔ ድሮ ትላንት እኔ ሳልፈጠር፣
አያት ቅድመ አያቴ በኖሩበት ዘመን፣
ድንቅ ሃብት ነበረች በትውፊት ያገኘኋት፣ 
ለእኔ ለልጃቸው በውርስ ያቀበሏት። 
ካላጠፏት በቀር ጨርሳ የማታልቅ፣
ብትበራ ብትበራ መሰልቸት ያማታውቅ፤
ውብ ሻማ ነበረች ለእኔ የተሰጠች፣
ለትንሽ ጎጆዬ ብርሃን የለገሰች ።
በቤቴ ማዕዘን በአንድ ጥግ በኩል፣
ንፋስ እየገባ እያየሁ ዝም ስል፣
ያልደፈንኩት ስተት እየባሰ መጥቶ፣
ድንቅ ስጦታዬን ክፉኛ  አሰቃይቶ፤
ድንገት አንድ ምሽት ብርሃን በሌለበት ፣
ጨረቃ ከዋከብት በማይታዩበት ፣
መታገል ያቃታት ያች ውብ ሻማዬ፣
ቀልጣ ቀልጣ ቀረች ውርሥ ስጦታዬ።

Saturday, March 11, 2017

🎉በእንተ ተሀድሶ

ትላንት ሥር ነቀል ለውጥ አዕላፍ ያደረቀ፣
ዛሬ “ተሀድሶ” ከሲዖል ጨለማ ዘልቆ የጠለቀ፤
ፍርሀት የወለደው የቅዠት አዝመራ፣
ጽጌረዳ አብቦ ሆምጣጤ ሚያፈራ፣
በጥማተ ወንበር ዙሪያ ገባው ታጥሮ፣
ቅጠሉ ዕፀ ሕይወት ግንዱ የጎመሮ፤