Thursday, July 16, 2015
Saturday, July 11, 2015
የፍጻሜ ልዑል
የፍጻሜ ልዑል
በገፍ እየጠጣ ወንዝ እና ዝናሙን ባህሩ ካልረካ፣ በጅምላ እያቀፈ ፀሐይ ከዋከብቱን ጠፈሩ ካልፈካ።
በቀረብነው ቁጥር ግባችን ከራቀ፣
የተጀመረ እንጅ ባይኖረን ያለቀ፣
ጣእመ ህላዌ እንዳይሆን መራራ፣
ቅስም እንዲያንሰራራ፣
መሃላችን ካለ
ባ'ለ ብዙ ጅምር ባለ ሺህ ሙከራ፣
ምንቸት እና ጋን
ይኑር እንጅ ባ'ገር፣በቀየ በሰፈር፣
ኩሬ ሙሉ ዉሃ ምድጃ ሙሉ እሳት
ዳውላ ሙሉ አፈር፤
የምንቸቶች ስፍር መች በጋን ይለካል፣
ጋኖች እንኳን ቢያልቁ ሌላ አፈር ይቦካል።
ምንጭ፦ ስብስብ ግጥሞች
በውቀቱ ስዩም
Subscribe to:
Posts (Atom)