እና እደነገርሁሽ
የረዚደንት ቁጣ አይቶ መሳቀቁ
ሲኔር መጣ አልመጣ ሰውነት ማለቁ
ፖርተር ማፈላለግ ከነርስ መዳረቁ
ዱቲ አድሮ ለሞርኒንግ ሽር ጉድ ማለቱ X ray ማስነሳት BF ማሰራቱ የወለደች እናት ጫማ መፈለጉ ሞቶ የወጣን ፅንስ "alive" ማድረጉያለ ዲሰፖዜብል ቪጎ ማስተካከል ካቴተር መንቀሉ የደሞዝ ቅናሹን አምኖ መቀበሉ ምን ብዬ ልንገርሽ ያማል ይሄ ሁሉ ታማሚ አስታሚ ወላጅ አስወላጁ አጥማቂ ሰቫኪው አስቀዳሽ ሰጋጁ የፈቃድ ባርነት በአንድነት ሲያውጁ ጨካኝ በበዛባት በዚች የምጥ ዓለም
ከዚህ የበለጠ ሌላ ህመም የለም
ጌች ቀጭኑ ዘታችቤት 02/09/10
ጭቅጭቁ ያማል
ንትርኩ ያማል
በዚህ ሁሉ መሃል
ምርኮኛሽ ጧት ማታ ከደጅሽ ይቆማል
በርሽ ተንበርክኮ
ብሶቱን ያሰማል
የሠናፍጭ ቅንጣት በምታክል እምነቱ ተራራው ይገፋል
የማያልፍ ቀን የለም የጭንቁም ቀን ያልፋል
ይሄን ጊዜ ታዲያ
ይሄን ጊዜ ታዲያ
የማረክሽው ልቤ እርጥብ በሚያቃጥል የፍቅርሽ
ነበልባል
ፀጉሩ ያላረረ የእንባ መስዋዕትን ለክብርሽ ያቀርባል
እና እንደነገርሁሽ እኔ አንችን ስወድሽ
ይኸን ሁሉ ችዬ ነው የምላመድሽ
እና እንደነገርሁሽ
የ“quali” ማዕበል ወጀቡ ቢንጠኝ
ዓመት ሙሉ አንብቤ grade C ቢሰጠኝ
ችግር ቢደራረብ መከራ ቢበዛ
ማርክ በዳሌ ቢሆን በከንፈር ቢገዛ
እኔ አንችን ስወድሽ
ይሄን ሁሉ ችዬ ነው የምሳደድሽ
ኦ እናት medicine ፀሊም ወፀዓዳ
ጽዋሽ የማያልቀው ቢቀዳ ቢቀዳ
መዛመድ ሳያንስሽ ተግባርሽ የባዕዳ
ከጦርነት ማግስት ቦምብሽ ሚፈነዳ
ኦ እናት medicine እናት ህክምና
ይሻልሻል ብዬ ከአምና ከታቻምና
ወጣት ልጅነቴን
ክብር ማንነቴን
ቆንጥሬ ሳላስቀር ጠቅልዬ ሰጥቸሽ
ገዝግዘሽ ገዝግዘሽ ቆርጠሽኝ ሰለቸሽ
ኦ እናት medicine ፀሊም ወፀዓዳ
መዛመድ ሳያንሰን ተግባርሽ የባዕዳ
የዓርነቴ ፀሐይ የነፃነቴ ጎህ እያልሁሽ ስመካ
ፍቅርሽ አሲምፕቶት የሚጠጉት እንጅ በዕጅ የማይነካ
ጽዋሽ የማያልቀው ቢቀዳ ቢቀዳ
መዛመድ ሳያንስሽ ተግባርሽ የባዕዳ
ከጦርነት ማግስት ቦምብሽ ሚፈነዳ
ኦ እናት medicine እናት ህክምና
ይሻልሻል ብዬ ከአምና ከታቻምና
ወጣት ልጅነቴን
ክብር ማንነቴን
ቆንጥሬ ሳላስቀር ጠቅልዬ ሰጥቸሽ
ገዝግዘሽ ገዝግዘሽ ቆርጠሽኝ ሰለቸሽ
ኦ እናት medicine ፀሊም ወፀዓዳ
መዛመድ ሳያንሰን ተግባርሽ የባዕዳ
የዓርነቴ ፀሐይ የነፃነቴ ጎህ እያልሁሽ ስመካ
ፍቅርሽ አሲምፕቶት የሚጠጉት እንጅ በዕጅ የማይነካ
ጎጻጉጽሽ ብዙ ቢሆን በዚች ዓለም
እኔ አንችን ከመውደድ የሚያግድ አይደለም